ገፆች

ረቡዕ 30 ኦገስት 2017

ኢትዮጵያ ሳይንስን በተመለከተ የት ላይ ነው ያለችው

ይህን ለመመለስ አንድን ሃገር ከሌሎች ጋር ለማነፃፀር የሚያስችለን መመዘኛ ያስፈልገናል። ለምሳሌ የኢኮኖሚ ይዘት ለመለካት የሃገሪቷ ጠቅላላ ምርቶችንና አገልግሎቶችን  የገብያ ዋጋ ተምነን (GDP)፣ ይህ ግምት በየዓመቱ የሚያሳየውን ለውጥ ማየት እንችላለን። በዚህ መመዘኛም ኢትዮጵያ ስምንት ከመቶ እድገት በማሳየት ዓለም ላይ በ5ኛ ደርጃ ትገኛለች።
ሳይንስንም በተመለከተ መጀመሪያ የምናየው መመዘኛ ለሳይንስ ምርምር የሚውልውን የገንዘብ መጠን ሲሆን፣  እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2013 ዓ.ም. ኢትዮጵያ 790 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እውላለች። በተቀራራቢ ወቅት ሌሎች የአፍሪካ ህገሮችን ስናይ የግብጽ 6.2 ቢሊን፣ ደቡብ አፍሪካ 4.8 ቢሊይየን እንዳዋሉ ይታያል። እንዲሁም ሌሎች - አሜሪካ 473.4 ቢሊየን፣ ቻይና 409 ቢሊየን፣ ጃፓን 179.8 ቢሊየን፣ ጀርመን 109.4 ቢሊየን፣ ደቡብ ኮርያ 91.6 ቢሊየን እና ህንድ 66.5 ቢሊን ተመዝግበዋል።
ሌላው መመዘኛ ከላይ የጠቀስነውን የአንድ ሃገር ጠቅላላ ምርቶችንና አገልግሎቶችን  የገብያ ዋጋ ተምነን፣ ከዚህም የገንዘብ መጠን ምን ያህል ድርሻው ለሳይንስ ምርምር እንደሚያውል መመልከት እንችላለን። አሁንም በአፍሪካ ያሉት ኢትዮጵያ 0.61 ከመቶ፣ ግብጽ 0.68 ከመቶ፣ ደቡብ አፍሪካ 0.73 ከመቶ እና እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ያሉት አሜሪካ 2.7 ከመቶ፣ ቻይና 2.1 ከመቶ፣  ጃፓን  3.6 ከመቶ፣ ጀርመን 2.9 ከመቶና ደቡብ ኮርያ 4.3 እያለ ይሄዳል።
ሌላ መመዘኛ ስንፈልግ ከፈተኛ ደረጃ ያላችው የሳይንስ ምርምር ውጤቶችን የሚዘግቡ ህትመቶችን መመልከት ይቻላል።  ክሃገራችንም እናዚህ ህትመቶች ላይ በየዓመቱ ለመቅረብ የበቁ ጥናቶች ብዛት  እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2013 እስከ 2016 ባለው ጊዜ የኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ6 እስከ 13 ሲሆኑ፣ ደቡብ አፍሪካ  ከ316 እስከ 584 ግብጽ  ከ51 እስከ 125፣ ኬንያ  ከ24 እስከ 28 ይታያሉ። ለመጥቀስ ያህል በዚህ መመዘኛ አንደኛ ላይ ያልችው አሜሪካ  ከ18727 እስከ 27300 ምርምሮች ለህትመት ያበቃች ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ምትገኘው ቻይና  ከ4511 እስከ 9673 አስመዝግባለች ።
እነዚህን መመዘኛዎች ስንመለከት ቁጥሮቹ እንደ ሃገራችን ኢኮኖሚ ዕድገቷ የታየውን ያህል ይሚያረኩ አይደሉም። ሆኖም በሃገራች ን በትምህርት እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጊ ዙሪያ የተቀረጹትን ፖሊሲዎች ስናይ፣ ለዕድገታችንና ለህዝባችን ደህንነት ዘርፉ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ሃመኔታ እንዳለን ያሳያሉ። ውጤታማ ለመሆን ግን ልክ በኢኮኖሚው ዘርፍ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020 መካከለኛ ገቢ ሃገር ለመሆን ዓላማ እንዳደረግንው ሁሉ፣ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱን ወይም ሌላ ተመሳሳይ  መመዘኛ መርጠን  በተወሰነ ጊዘ ውስጥ መድረስ የሚገባንን ግብ  ወስነን፣ ዓላማውን ለማሳካት ከፍተኛ መፍጨርጨር ማረግ ይገባን ይሆናል። ለምሳሌ ያህል በምርምር ህትመቶች ከአፍሪካ ሃገሮች ቀዳማዊ ደርጃን በአምስት ዓመት ውስጥ ለማያዝ ማቀድ ጥሩ መለስተኛ ግብ ሊሆን ይችላል።
፣የተጠቀሱት መረጃዎች የተገኙት ከድህረመረቡ ዊኪፔዲያና(www.wikipedia.com) ከኔቸር ህትመቱ ኔቸር ኢንዴክስ(www.natureindex.com) ነው።