በክፍል
1ሃ ለአቶም
መኖር መረጃ ያልኩትን ብራውኒያን እንቅስቃሴ
(Brownian Motion) መጀመሪያ
ከተመለከትኩበት የልጅነት ዕድሜዬ ብዙ ዓመታት
ያለፉ ሲሆን፣ አሁን ለትውስታ በድጋሜ ለማየት
ሞክሬ ውጤቱንም ከታች ባለው ምስል ለማስተላለፍ
ሞክሬያለሁ። ቅንታት የዱቄት ወተት በውሃ
በመበጥበጥና ትንሽ ያህሉን ምስሉ ላይ እንደሚታየው
የማጉያ መነጽር ስላይድ (Microscope
Slide) በሚባል መስታውት
ላይ በማድርግ፣ ዲጂታል ካሜራ በተገጠመለት
ማጉያ መነጽር አማካይነት በኮምቲዩተራችን ልናይበት በምንችለው በፊልም መልክ ከዚህ
ልጥፍ ጋር አያይዣለሁ። በትኩረት ሰንመለከት
ጠቆር ያሉ የመንቀጥቀጥ ዓይነት እንቅስቃሴ
የሚያሳዩ አካሎች የሚታዩ ሲሆን፣ እነዚህም
በጣም ጥቃቅን የወተቱ ብናኞች ሲሆኑ ሊታዩ
በማይችሉት በውሃው አቶሞች በመገጫጨታችው
ነው በዚህ መልክ ሊጨፍሩ የቻሉት። መልካም
ዕይታ!