ቀደም
ባሉ ልጥፎች ስለአቶም መኖር ያሉንን መረጃዎች
ከዘረዘርን፣ ስለ መጠናቸውስ ምን ማለት
ይቻላል? ከአቶሞች
ሁሉ ትንሹ ሃይድሮጅን (Hydrogen) የተባለው
ሲሆን በነጠላ መልኩ በተፈጥሮ በብዛት ባናገኘውም፣
የመኪና ባትሪ አፈላ ሲባል የሚፍለቀለቀው
ጋዝ እሱ ሲሆን፣ ስፋቱ አንድ መቶ ፒኮ ሜትር
ነው ። አንድ ፒኮ ሜትር አንድ ሜትር በአንድ
ትሪሊዮን (1,000,000,000,000) ሲካፈል
ወይም በአንድ ሚሊየን ሚሊየኖች ሲካፈል
የምናገኘው ርዝመት ነው። እንዚህን ዓይነት
ቁጥሮች በአዕምሮአችን መታዘብ በጣም አስቸጋሪ
ቢሆንም ከረቂቁ ተነስቶ እስከ ግዙፉ ለመረዳት
ስንፈልግ በሳይንሱ ዘርፍ መላልሰው ይገጥሙናል።
ለሎቹስ አቶሞች?
እንደ
አሮፓውያን አቆጣጠር በ 1866 ዓ.ም. ዲሚትሪ
ሜንዲሌቭ የተባለ ሩሲያዊ ሳይንቲስት በተለያየ
ጊዜ የተገኙትን የአቶም ዓይነቶችን በክብደታቸውና
ከሌሎች አቶሞች ጋር ከመዋሃድ ዝንባሌያቸው
ተነስቶ በሰንጠረዥ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ
አስቀመጣቸው። ሰንጠረጅም ፒሪዮዲክ ቴብል
(Periodic
Table) ተብሎ
ሲጠራ፣ የእያንዳንዱን ኢለመንት ስምያ በአንድ
ወይም በሁለት ፊድል በማሳጠር በሚከተለው
ምስል መልክ አስቀምጧል።
![]() |
ክ sciencenotes.org የተገኘ |
በልጥፉ
ከዚህ ስንቀጥል አንድ ዓይነት አቶም ብቻ የያዙ
ንጥረ ነገሮችን ኤሌሜንት (Element) ብለን
ስንጠራ፣ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የያዙትን
ደግሞ ኮምፓውንድ (Compound) እንላቸዋለን።
እስካሁን ድረስ በምድር (እና
እስከምናቅው ድረስ ከምድር ውጭም )
118 ብቻ
የተለያዩ ኤሌሜንቶች ሲኖሩ፣ እነዚህም ሲዋህዱ
እጅግ በጣም ብዙ ኮምፓውንዶችን ይፈጥራሉ።
እዚህም ላይ መጥቀስ የሚኖርብኝ አብዛኛው
በምድር ላይ የምናየው የአቶሞች ዉደህት ወይም
ኮምፓውንድ ሲሆን አልፎ አልፎ ግን ንጽህ
ኤሌሜንቶች ልናገኝ እንችላለን።
አንዳንድ
በየቀኑ ልናያቸው የምንችላችው ኤሌሜንት እና ኮምፓውንድ ለመጥቀስ ያህል፣ ሃይድሮጅን
ከላይ እንዳየነው፣ የምንተነፍሰው አየር
የኦክሲጅንና ናይትሮጅን ኤለመንቶችን ሲይዝ
ካርቦን ዳዮክሳይድ የተባለውን ኮምፓውንድ
ጨምሮ ሁሉንም ቀላቅሎ በጋዝ መልክ ይይዛል።
እጅግ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ መጨረሻ የተጠቀሰውን
ካርቦን ዳዮክሳይድ (Carbon
Dioxide) ዕጽዋቶች
ከጽሓይ ብርሃን በሚያገኙት ሃይል አማካይነት
ከውሃ ጋር በመቀላቀል፣ ወደ ጠጣሩ ቅጠልና
ግንድ የሰውነት አካላቸው የመቀየር ችሎታ
አላቸው። የተላያዩት ብረቶችም በአብላጫ
ንጹህ ኤሌመንት ሊሆኑ ይችላሉ።
አሉሚኒይም (Aluminum) ከነዚህ
ብረቶች በምድር ላይ ከፍተኝውን ድርሻ ሲይዝ
ሁለተኛውን ደርጃ ደግሞ በልምዳችን ብረት
ብለን ይምንጠራውና አሁን በጣም በሃገራችን
ተፈላጊ የሆነው አይረን (Iron) ለመኪና፣
ለኮንስትራክሽን ዘንግ ውዘተ የምንጠቀምበት
ሲሆን፣ መዳብ ወይም ኮፐር(Copper) ኤሌትሪክ
ሽቦ ላይ፣ ወርቅ እና ብር ደግሞ በምንጋጌጥባቸው
ይጋኛሉ። ሲሊኮን (Silicon) የተባለው
ከሁሉም ኤለመንቶች ምድር ላይ በመብዛት አንደኛ
ደረጃ የያዘ ሲሆን ከኦክሲጀን ጋር ተቀላቅሎ
መስታውትን ሲሰራ፣ በንጹህ ኤለመንት መልኩ
ደግሞ በኤሌክትሮኒክ መሥሪያዎች ሁሉ ዋነኛ
የሆኑትን ትራንዚስተርና አይሲ እንድንሰራ
በማስቻሉ ትልቅ ባለውለታችን ነው። ብዙ ሌሎች
መጥቀስ ቢቻልም እጅግ በጣም በጣም ለእኛ ያለው
ጥቅምን ይሚገልጽ ቃል የሚታጣለት፣ የኮከቦች
ኮከብ ኤለመንት፣ ነፍስ ላላው ነገር ሁሉ
መሠረት የሆንው ካርበን (Carbon) ሲሆን፣
በተለያዩ መልክና ይዘቶች እናየዋለን። በንጹህ
መልኩ በአንድ በኩል የምንጋጌጥበት አልማዝ
በሌላ ደግሞ በድስት ላይ በምናገኘው ጥላሸት
ሲታይ፣ በተለይ ከሃይድሮጅንና ከኦክሲጀን
ጋር ተዋህዶ የኛንና የለሎች ነፍሳት አካል
ዋናውን ክፍል ይይዛል።
በክፍል
ሶስት ለጥፍ ስለ ካርበንና በሱ ላይ የተመሠረቱትን
ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ የሚገነቡ
ኮምፓውንዶችን እንመለከታለን።