ገፆች

ረቡዕ 26 ጁን 2024

ረቂቁ አቶም (ክፍል 3ለ) - ውህዶች ምን የመስላሉ

 

አንድን ነገር ለመረዳት ስንፈልግ ካሉን ስሜቶች በከፍተኛ ደረጃ የምንጠቀመው የማየት ችሎታችንን ነው። በተጨማሪም የመስማት የመዳሰስና የመቅመስ ችሎታዎቻችንን እንጠቀማለን። ነገር ግን እንዚህ ችሎታዎቻችን በቀጥታ አቶሞችንን ለመረዳት አልጠቀሙንም። ቀደም ሲል የአቶሞችን መኖር የደረስንበት የአንዳንድ ነገሮችንን ጉልህ ባህርይ በማጥናትና፣ ቀጥለንም የማሰብና የማመዛዘን ችሎታችንን ተጠቅመን፣ እንዴት ቢሆን ነው እንዚህን ባህርዮች ሊፈጠሩ የቻሉት ብለን በመጠየቅ ነው። በዚህም ዓይነት ሁሉም ነገሮች እጅግ በጣም ረቂቅ በሆኑ አቶሞች እንደተሠሩ የደረስንበት።

አቶሞችን መመልከት የሚከለክለን ረቂቅነታቸው ብቻ አይደለም። ምንም ዓይነት እዚህ ጀምሮ እዚህ ያልቃል የምንለው ጠጣር ይዘት የላቸውም። ነገር ግን በውስን መልኩ ለመረዳት፣ አቶሞችን የተለያየ መጠን ያላችው በጣም ትናንሽ እንደ ኳስ ክብ የሆኑ አካላት መቁጠር እንችላለን። ቅጥለንም ኳሶቹን በተለያየ መንገድ በመቀጣጠል ውህዶችን ለመግለጽ መሞከር እንችላለን።

ለምሳሌ ውሃን ብንመለከት፣ አንድ የውሃ ውህድ አንድ ኦክሲጅንና ሁለት ሃይድሮጅን አቶም ይይዛል። ይህንንም እንደሚከተለው መግለጽ ይቻላል።

ውሃ

በዚህ ምስል መሃል ላይ በቀይ ኦክሲጅንን ከጎኑ ደግሞ በነጭ ሁለቱን ሃይድሮጅኖች እናያለን። ሃይድሮጅኖቹ መጠናቸው አንስ እንደሚሉና እንዲሁም ሶስቱ አቶሞች ቀጥ ባለ መስመር ላይ ሳይሆን ሸፈፍ ብለው እንደተቀመጡ እንናስተውላለን።

ሁለት ሌሎች ምሳሌዎች ፕሮፔን የተባለውን የሲሊንደር ጋዝንና በሰውነታችን የሚገኘው ግሉኮዝን ብንመለከት ፕሮፔን ሶስት ካርበንና 6 ሃይድሮጅን የያዘ ውህደት እንደሆነና፣ ግሉኮስ ደግሞ 6 ካርበን 6 ኦክሲጅንና 12 ሃይድሮጅን መያዛቸውን እናያለን።

ፕሮፔን

ግሉኮዝ

እነዚህ ምሳሌዎች አነስ ያሉ ውህዶች ሲሆኑ፣ በሰውነታችን የሚገኙት ግን በመቶዎች ወይም በሽህዎች የሚቆጥውሩ አቶሞችን ሊያካትቱ ይችላሉ። በደማችን ሂሞግሎቢን ተብሎ የሚጠራውና የደም ማነስ ሲኖርብን መጠኑ ቀንሶ የምናገኘው ፕሮቲን ከ4000 በላይ አቶሞችን ያካተተ ውህድ ሲሆን ከታች የምንመለከተውን ቅርጽ የያዘ ነው።

 

ሂሞግሎቢን

የስብ ውህደት ደግሞ በደማችን ሲለካ ትራይግሊሴራይድ ተብሎ የሚጠራው የሚከተለውን ይመስላል።

ትራይግሊሴራይድ

የነዚህን ውህዶች መጥን ስንመለከት ደግሞ፣ የውሃው ውህድ ካንድ የታይፕ ወረቀት ቅጥነት በሚሆን ወደ 350 ሚሊየኑን ማስቀመጥ ስንችል፣ በዚያው ስፋት ውደ 20 ሚሊየን ሂሞግሎቢን ማስቀመትጥ እንችላለን። ክብደተቸውን ስንመለከት ይውሃው ውህደት በአንድ ግራም ሰላሳ ሺህ ቢሊየን ቢሊየን (322 ዜሮ) ውህዶች ሲይዝ ዘጠኝ ቢሊየን ቢሊየን (918ዜሮ) ሂሞግሎቢን ውህዶችችን ማካተት ይችላል።

የደም ማነስ ሲጠረጠር በደማችን የሂሞግሎቢን መጠን የሚለካ ሲሆን፣ ኖርማል በሚሆንበት ጊዜ በአንድ የደም ጠብታ በአማካይ 7.5 ሚሊግራም (የአንድ ግራም አንድ ሺኛ) ሲገኝ፣ ይህም ወደ ስልሳ ሚሊየን ቢሊየን (616 ዜሮ) ውህዶችን ያካትታል።

በሰውነታችን የሚገኙ ውኡህዶችን ከላይ ባየነው መልክ የንጥረ ነገር ይዘታቸውንንና እንዲሁም ቅርጻቸውን በሚገባ የመረዳት አስፈላጊነቱን ደግሞ በሚቀጥለው ልጥፍ እንመለከታለን።