በጤና
ሳይንስ ዘርፍ የአንድን ህመም መነሻን ለመረዳት
ስንል ብዙ ጊዜ ሚገጥም ጥያቄ - ይህ
ህመም ከዘር በሚተላለፍ ጉድለት ነው አመጣጡ፣
ወይስ ከወሊድ በኋላ ከሚገጥሙን ከአካባቢያችን
ወየም ከአኗኗራችን ከመነጩ ምክኒያቶች ነው
ሊከሰት የቻለው የሚለው ነው። ከዘር ጉድለት
የሚከሰተውን ለመከላከል ማረግ የምንችልው
ውስን ሲሆን፣ ከአካባቢያችን ችግር ለሚከሰቱት
ግን የተለያዩ እርምጃዎች የመውሰድ ዕድል
ሊኖረን ይችላል ።ለምሳሌ
ያህል እንደ ውባ ያሉት ተላላፊ ህመሞች መንሰኤ
ሙሉ በሙሉ ከአካባቢያችን የምንጋፈጣቸው
ጅርሞች ሲሆኑ፣ በሃገራችን ብዙ የማይታዩት
ሲስቲክ ፋይብሮሲስና (Cystic
Fibrosis) ፌኒልኬቶንዩሪያ (Phenylketonuria) የተባሉት
ደግሞ ሙሉ በሙሉ በዘር ከሚተላለፉ ጉድለቶች
የሚመጡ ናቸው። በርካታ ህመሞች ግን ሙሉ በሙሉ
ከዘር ወይም ከአካባቢ ብለን በእርግጠኝነት
መለይት አንችልም። ይልቅ ከዘር የሚተላለፉ
ጉድለቶች ለአንዱ ወይም ለሌላው ህመም የሚያጋልጡን
ሲሆን፣ ህመሙ እንዲከሰት ግን ተጨማሪ
ከአካባቢያችን ወይም ከአኗኗራችን ጋር የተያያዙ
ምክኒያት ወይም ምክኒያቶች ጋር መግጠም
ይኖርበታል። በዚህም ዓይንት የሚከሰቱ የጡት
ካንሰርና በአዋቂውች የሚታየው የስኳር በሽታ
የገኛሉ።
ከህመም ሌላ ግን ከዘርም ከአካባቢም ተዕጽኖዎች የተለያየ መጠን ሊኖራቸው የሚችሉት የሰውነታችን ውፍረትና ቁመት ልክ ናቸው። በተለይም ብዙዎቻችን የልጆች ውፍረት መጠን ወላጆች በልጆቹ ላይ የሚተገብሩት የአመጋገብ ስርዓትን (ማለትም ከዘር ይልቅ ከአካባቢ ወይም ከአኗኗር) ያንጸባርቃል ብለን እናምናለን። ግን ምን ያህል እርግጠኛ መሆን እንችላላን?የህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ በጣም ጠቃሚ ሆኖ የተገኘው አንደኛው ሳይንሳዊ የጥናት ዘዴ የመንትዮሽ ጥናት (Twin Studies) የተባልውን በመጠቀም ነው። መንታዎች ሁለት ዓይነት ናቸው፣ ተመሳሳይ የሆኑና (Identical) ተመሳሳይ ያልሆኑ (Non-identical)። ተመሳሳይ የሆኑ መንታዎች የሚፈጠሩት ከአንድ የወንዴና ከአንድ የሰቴ የዘር ፍሬ ውህደት የተጸነሰው ህዋስ አንድ ልጅ መፍጠር ሲጠበቅበት ተከፋፍሎና ተለያይቶ ሁለት (አንዳንድ ጊዜ ከሁለትም በላይ) ለጆች ሲያስከትል ነው - ከወላጆቻቸው የሚወርሱት ዘርም አንድ ዓይንት ነው። ተመሳሳይ ያልሆኑት ግን ከሁለት የወንዴና ከሁለት የሰቴ የዘር የተጸነሱ ሲሆን፣ በተለያየ ጊዜ ከተወለዱ ለጆች ብዙ አይለዩም - ዘራቸውም አንዳንድ ጊዜ ጾታቸውም የተለያየ ነው። ስንቀጥልም ያአንድን ህመም ወይም ባህርይ በህብረተሰቡ ያለውን ስረጭት ብንመለከት፤ ከተመሳሳይ መንታዎች በአንዱ ውይም በሁለቱ ላይ የሚታይብት ጊዜ ከማይመሳሰሉ መንትዮች ወይም መንታ ካልሆኑ ልጆች ጋር ተመጣጣኝ ከሆነ፤ መንስኤው ከዘር እንዳልሆነ መደምደም እንችላለን። በአንጻሩ በሁለቱም ተመሳሳይ መንትዮች የሚታየበት ጊዜ ከሌሎቹ አብላጫ ካሰየ ግን ከዘር የመተላለፍ ዝንባሌ እንደሚኖረው እንደመድማለን።
ወደ ልጥፉ ርዕስ ስንመጣ - በኪግክስ ኮሌጅ ለንደንና (Kings College London) በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለንደን (University College London) በመተባበር፣ በሳስኪያ ሴልዛም (Saskia Selzam) መሪነት የተሰራው ጥናት፣ የለጆች ክብደት መጠን ከወላጆች ከሚያገኙት አመጋገብ ጋር ያለውን ግንኙንት ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል። ይልቅ ወላጆች የሚከተሉት አመጋገብ ስልት በተገላቢጦሹ የለጆቹን የውፍረት መጠን የሚከተል ሲሆን ይህ መጠን ደግሞ በአብላጫው በዘር የሚወሰን እንደሆነ ደምድመዋል። "ጥናታችን የሚያሳየን ወላጆች የሚከተሉት የአመጋገብ ስርዓት የልጆቹን ወፍራም ወይም ቀጭን የመሆን ከዘር የመጣ የተፈጥሮ ዝንባሌን የተከተለ ነው" ብለዋል።እዚህም ድምዳሜ ላይ የደረሱት ክ1994 እስከ 1996 በእንግሊዝ ሃገር የተወለዱ 4500 ጥንድ መንትዮችን በማጥናት ነው። ሳይንቲስቶቹ ጥናቱን የሠሩት የልጆች የክብደት መጠን በየጊዜው እየጨመረ ለመሄዱ ዝንባሌ ምክኒያት ሊሆኑ የሚችሉ የአካባቢ ተዕጽኖዎችን ለመለየት ሲሉ ነው። እስካሁን ባለን ልምድ የሚበሉትን መጠን እንዲቀንሱ ጫና ሚደረግባቸው ልጆች የመወፈር ዝንባሌ እንደሚኖራቸው (ቁጥጥር በሌለበት ሰዓት የተከለከለ ነገር ሁሌ ስለሚያምረን ያጡት የመሰላቸውን ላማካካስ ስለሚጥሩ) ፣ እንዲጨምሩ የሚጫኗቸው ደግሞ ከመናሻው አነስተኛ የምግብ ፍላጎት ያላቸው ልጆቹ ላይ ጭንቀት ስለሚያስከትል እንዲያውም የበለጠ የምግብ ፍላጎታቸውን እንደሚያዳክም ይገመታል። ነገር ግን ደግሞ የሰውነታችን ውፍረት መጠን በዘር የመተላለፍ ዝንባሌ እንዳለው ጥናቶች ያመላክታሉ። ይህም ጥናት በተጨማሪ የሚይመለክተው ወላጆች ይህንን ከዘር እሚገኘውን ዝንባሌ በመከተል ነው የአመጋገብ ሥራዓታቸውን የሚያስተካክሉት እንጂ እንደምናስበው ከየራሳቸው ተነሳሽነት ውይም ጸባይ የሚወሰን አይደለም። ጥናቱም መንትዮቹ በዘር የሚወርሱትን የመወፈር ዝንባሌን (ዲ ኤን ኤ – DNA) መርምረው ይሕም ከላይ የተገለጸውን ወልጆች በልጆቻቸው ላይ ከሚተገብሩት የአመጋገብ ሥራዓት ጋር እንደሚዛመድ አረጋግጠዋል።
ይህ ጥናት የሚያስገነዝበን ልጆች በሚመገቡት መጠንና ቀጥሎም ለውፍረታቸው ወላጆች ያላቸው ሚና ወይም ተጠያቂነት ውስን እንደሆነ ነው (የምግብ እጦት ደረጃ መለስ)። ልጆቹ የሚመገቡትን መጠን በጥብቅ መቆጣጠር ጥቅም ወይስ ጉዳት ይኑረው ጥናቱ ሊነግረን አይችልም። ለረጅም ጊዜ ብዙ ልጆችን ከጨቅላ ዕድሜ እስክ ልጅናታቸው ማገባደጃ ድርስ የሚከታተል ጥናትም (Longitudinal Study) ጉዳዩን የበለጠ ለመረዳት ያስችለናል ሲሉ አጥኚዎቹም ጽሁፋቸውን አጠቃለዋል።

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ