ገፆች

ረቡዕ 20 ማርች 2019

ከሳይንስ አድማስ (02-2011) - ሳይንስ ሶሺያል ሚዲያና ፖለቲካ



ሶሺዮሎጂ (Sociology) - የህብረተሰብ ጉዳዮችን በሳይንሳዊ አካሄድ ማጥናት ሲሆን፣ ከሶሺያል ሳይንሶቹ (ታሪክ፣ ጂዮግራፊ፣ ፖሊቲካል ሳይንስ፣ ምጣኔ ሃብት ጥናት ወዘተአንደኛው ዘርፍ ነው። በህብረተሰብ ውስጥ የሚታዩ ግንኙነቶች፣ ባህሎች፣ ባህሪዮችን በዚህ መልክ በማጥናት የሚገኙት መረጃዎችም ፖሊሲ ለማርቀቅና ለማቀድ ጠቃሚ ግባዓት ሊሆኑ ይችላሉ። ባአሁኑ ውቅት ደግሞ ድረ መረብ ላይ ያሉ ሶሺያል መዲያ (Social Media) በሚሊዮን የሚቆጠሩ የህዝብ አስተያየቶችን፣ ሃተታዎችን፣ አመለካከቶችን በኮምፒዩተር እገዛ አጣርቶ ለመመርመር አመቺ በሆነ መልኩ በማስቀመጥ፣ ከዚህ ቀደምሊታሰብ ባልተቻለ መልኩ ለሶሺዮሎጂ ተመራማሪውች ትልቅ ዕድል ፈጥሯል። ይህንንም ዕድል በመጠቀም በቱዊተር (Twitter) የሚተላለፉ ሃሰተኛ መርጃ አሰረጫጭትን በተመለከተ ሶስት ተመራማሪዎች (ቮሱጊ፣ ሮይና አራል የተባሉያደረጉትን ጥናት ውጤት በሳይንስ ምጽሄት (Science 359, 9th March, 2018) ይፋ ተደርጓል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2006 እስከ 2017 .በቱዊተር ይተላለፉ ዕውነተኛና ሃሰተኛ ልጥፎችን ተመለከተዋል። በዚህም ወቅት በሶስት ሚሊየን ሰውች አራት ተኩል ሚሊየን ጊዜ የተላለፉ ልጥፎችን መርምረዋል። የእውነተኝነት ውይም ሃሰተኝነት ይዘታቸውን ለመለየት ስድስት የተላያዩ ገለልተኛ አጣሪ አካሎችን ግምገማ ተጠቅመዋል። በዚህም ጥናት የታየው ሃሰተኛ ይዘት ያላቸው ልጥፎች ከእውነተኞቹ በበለጠ ፍጥነትና ስፋት መሰራጨታቸውን አረጋግጠዋል። ከዚህም በተጨማሪ የልጥፎቹን መልዕክት ሲመለከቱ የፖለቲካ የዘት የያዙ ሃሰተኛ ልትፎች ከሌሎቹ ስለሽብር፣ ተፈጥሮ አደጋ፣ ሳይንስ፤ የከተማ ወሬና ስለንግድ መረጃ የዘት ካላቸው የሃሰተኛ ልጥፎች ሲነጻጸር ከሁሉም በበለጠ ደረጃ መሰራጨታቸውን አረጋግጠዋል። በሶሺያል ሚዲያ የሚተላለፉ መልዕክቶች ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ተዕጽኖ ሊኖራቸው እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ለምሳሌ ያህል ፕረዚደንት ኦባማ በፈንጂ ቆስለዋል በሚል ሃሰተኛ መልዕክት በስቶክ ግብይት (Stock Market) ላይ በነበረው ተዕጽኖ መቶ ሰላሳ በሊየን ዶላር የሚገመት ኪሳራ አድርሷል። በቅርብ ጊዜ ቢቢሲ የዘገበውም በሜክሲኮ ሃገር በዋትሳፕ (WhatsApp) ልጆችን አግትዋል ተብሎ በተላለፈው ሃሰተኛ መረጃ ምክኒያት በተቀሰቀሰ ቡድን ሁለት ግለሰቦች በእሳት ተጋይተው ሂወታቸው ሊያልፍ ችሏል። አንዳንድ ጊዜ በተለያየ ሃገር በሚኖረው የፖለቲካ አለመረጋት ወቅትም በሶሺያል ሚዲያ የሚሰራጭ ሃሰተኛ መረጃ ሊያደርስ የሚችለውን ቀውስ ስናስብ ምናልባት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል ብንል አይፈረድብንም። 


ማክሰኞ 26 ፌብሩዋሪ 2019

ረቂቁ አቶም (ክፍል 2)


ቀደም ባሉ ልጥፎች ስለአቶም መኖር ያሉንን መረጃዎች ከዘረዘርን፣ ስለ መጠናቸውስ ምን ማለት ይቻላልከአቶሞች ሁሉ ትንሹ ሃይድሮጅን (Hydrogen) የተባለው ሲሆን በነጠላ መልኩ በተፈጥሮ በብዛት ባናገኘውም፣ የመኪና ባትሪ አፈላ ሲባል የሚፍለቀለቀው ጋዝ እሱ ሲሆን፣ ስፋቱ አንድ መቶ ፒኮ ሜትር ነው ። አንድ ፒኮ ሜትር አንድ ሜትር በአንድ ትሪሊዮን (1,000,000,000,000) ሲካፈል ወይም በአንድ ሚሊየን ሚሊየኖች ሲካፈል የምናገኘው ርዝመት ነው። እንዚህን ዓይነት ቁጥሮች በአዕምሮአችን መታዘብ በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም ከረቂቁ ተነስቶ እስከ ግዙፉ ለመረዳት ስንፈልግ በሳይንሱ ዘርፍ መላልሰው ይገጥሙናል። ለሎቹስ አቶሞች?

እንደ አሮፓውያን አቆጣጠር በ 1866 .ዲሚትሪ ሜንዲሌቭ የተባለ ሩሲያዊ ሳይንቲስት በተለያየ ጊዜ የተገኙትን የአቶም ዓይነቶችን በክብደታቸውና ከሌሎች አቶሞች ጋር ከመዋሃድ ዝንባሌያቸው ተነስቶ በሰንጠረዥ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ አስቀመጣቸው። ሰንጠረጅም ፒሪዮዲክ ቴብል (Periodic Table) ተብሎ ሲጠራ፣ የእያንዳንዱን ኢለመንት ስምያ በአንድ ወይም በሁለት ፊድል በማሳጠር በሚከተለው ምስል መልክ አስቀምጧል።
ክ sciencenotes.org የተገኘ


በልጥፉ ከዚህ ስንቀጥል አንድ ዓይነት አቶም ብቻ የያዙ ንጥረ ነገሮችን ኤሌሜንት (Element) ብለን ስንጠራ፣ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የያዙትን ደግሞ ኮምፓውንድ (Compound) እንላቸዋለን። እስካሁን ድረስ በምድር (እና እስከምናቅው ድረስ ከምድር ውጭም ) 118 ብቻ የተለያዩ ኤሌሜንቶች ሲኖሩ፣ እነዚህም ሲዋህዱ እጅግ በጣም ብዙ ኮምፓውንዶችን ይፈጥራሉ። እዚህም ላይ መጥቀስ የሚኖርብኝ አብዛኛው በምድር ላይ የምናየው የአቶሞች ዉደህት ወይም ኮምፓውንድ ሲሆን አልፎ አልፎ ግን ንጽህ ኤሌሜንቶች ልናገኝ እንችላለን።
አንዳንድ በየቀኑ ልናያቸው የምንችላችው ኤሌሜንት እና ኮምፓውንድ ለመጥቀስ ያህል፣ ሃይድሮጅን ከላይ እንዳየነው፣ የምንተነፍሰው አየር የኦክሲጅንና ናይትሮጅን ኤለመንቶችን ሲይዝ ካርቦን ዳዮክሳይድ የተባለውን ኮምፓውንድ ጨምሮ ሁሉንም ቀላቅሎ በጋዝ መልክ ይይዛል። እጅግ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ መጨረሻ የተጠቀሰውን ካርቦን ዳዮክሳይድ (Carbon Dioxide) ዕጽዋቶች ከጽሓይ ብርሃን በሚያገኙት ሃይል አማካይነት ከውሃ ጋር በመቀላቀል፣ ወደ ጠጣሩ ቅጠልና ግንድ የሰውነት አካላቸው የመቀየር ችሎታ አላቸው። የተላያዩት ብረቶችም በአብላጫ ንጹህ ኤሌመንት ሊሆኑ ይችላሉ። አሉሚኒይም (Aluminum) ከነዚህ ብረቶች በምድር ላይ ከፍተኝውን ድርሻ ሲይዝ ሁለተኛውን ደርጃ ደግሞ በልምዳችን ብረት ብለን ይምንጠራውና አሁን በጣም በሃገራችን ተፈላጊ የሆነው አይረን (Iron) ለመኪና፣ ለኮንስትራክሽን ዘንግ ውዘተ የምንጠቀምበት ሲሆን፣ መዳብ ወይም ኮፐር(Copper) ኤሌትሪክ ሽቦ ላይ፣ ወርቅ እና ብር ደግሞ በምንጋጌጥባቸው ይጋኛሉ። ሲሊኮን (Silicon) የተባለው ከሁሉም ኤለመንቶች ምድር ላይ በመብዛት አንደኛ ደረጃ የያዘ ሲሆን ከኦክሲጀን ጋር ተቀላቅሎ መስታውትን ሲሰራ፣ በንጹህ ኤለመንት መልኩ ደግሞ በኤሌክትሮኒክ መሥሪያዎች ሁሉ ዋነኛ የሆኑትን ትራንዚስተርና አይሲ እንድንሰራ በማስቻሉ ትልቅ ባለውለታችን ነው። ብዙ ሌሎች መጥቀስ ቢቻልም እጅግ በጣም በጣም ለእኛ ያለው ጥቅምን ይሚገልጽ ቃል የሚታጣለት፣ የኮከቦች ኮከብ ኤለመንት፣ ነፍስ ላላው ነገር ሁሉ መሠረት የሆንው ካርበን (Carbon) ሲሆን፣ በተለያዩ መልክና ይዘቶች እናየዋለን። በንጹህ መልኩ በአንድ በኩል የምንጋጌጥበት አልማዝ በሌላ ደግሞ በድስት ላይ በምናገኘው ጥላሸት ሲታይ፣ በተለይ ከሃይድሮጅንና ከኦክሲጀን ጋር ተዋህዶ የኛንና የለሎች ነፍሳት አካል ዋናውን ክፍል ይይዛል።
በክፍል ሶስት ለጥፍ ስለ ካርበንና በሱ ላይ የተመሠረቱትን ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ የሚገነቡ ኮምፓውንዶችን እንመለከታለን።