ሶሺዮሎጂ (Sociology)
- የህብረተሰብ
ጉዳዮችን በሳይንሳዊ አካሄድ ማጥናት ሲሆን፣
ከሶሺያል ሳይንሶቹ (ታሪክ፣
ጂዮግራፊ፣ ፖሊቲካል ሳይንስ፣ ምጣኔ ሃብት
ጥናት ወዘተ) አንደኛው
ዘርፍ ነው። በህብረተሰብ ውስጥ የሚታዩ
ግንኙነቶች፣ ባህሎች፣ ባህሪዮችን በዚህ
መልክ በማጥናት የሚገኙት መረጃዎችም ፖሊሲ
ለማርቀቅና ለማቀድ ጠቃሚ ግባዓት ሊሆኑ
ይችላሉ። ባአሁኑ ውቅት ደግሞ ድረ መረብ ላይ
ያሉ ሶሺያል መዲያ (Social
Media) በሚሊዮን
የሚቆጠሩ የህዝብ አስተያየቶችን፣ ሃተታዎችን፣
አመለካከቶችን በኮምፒዩተር እገዛ አጣርቶ
ለመመርመር አመቺ በሆነ መልኩ በማስቀመጥ፣
ከዚህ ቀደምሊታሰብ ባልተቻለ መልኩ ለሶሺዮሎጂ
ተመራማሪውች ትልቅ ዕድል ፈጥሯል። ይህንንም
ዕድል በመጠቀም በቱዊተር (Twitter) የሚተላለፉ
ሃሰተኛ መርጃ አሰረጫጭትን በተመለከተ ሶስት
ተመራማሪዎች (ቮሱጊ፣
ሮይና አራል የተባሉ) ያደረጉትን
ጥናት ውጤት በሳይንስ ምጽሄት (Science
359, 9th March,
2018) ይፋ
ተደርጓል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር
ከ2006 እስከ 2017 ዓ.ም. በቱዊተር
ይተላለፉ ዕውነተኛና ሃሰተኛ ልጥፎችን
ተመለከተዋል። በዚህም ወቅት በሶስት ሚሊየን
ሰውች አራት ተኩል ሚሊየን ጊዜ የተላለፉ
ልጥፎችን መርምረዋል። የእውነተኝነት ውይም
ሃሰተኝነት ይዘታቸውን ለመለየት ስድስት
የተላያዩ ገለልተኛ አጣሪ አካሎችን ግምገማ
ተጠቅመዋል። በዚህም ጥናት የታየው ሃሰተኛ
ይዘት ያላቸው ልጥፎች ከእውነተኞቹ በበለጠ
ፍጥነትና ስፋት መሰራጨታቸውን አረጋግጠዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የልጥፎቹን መልዕክት ሲመለከቱ
የፖለቲካ የዘት የያዙ ሃሰተኛ ልትፎች ከሌሎቹ
ስለሽብር፣ ተፈጥሮ አደጋ፣ ሳይንስ፤ የከተማ
ወሬና ስለንግድ መረጃ የዘት ካላቸው የሃሰተኛ
ልጥፎች ሲነጻጸር ከሁሉም በበለጠ ደረጃ
መሰራጨታቸውን አረጋግጠዋል። በሶሺያል ሚዲያ
የሚተላለፉ መልዕክቶች ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ
ተዕጽኖ ሊኖራቸው እንደሚችል መገመት አያዳግትም።
ለምሳሌ ያህል ፕረዚደንት ኦባማ በፈንጂ
ቆስለዋል በሚል ሃሰተኛ መልዕክት በስቶክ
ግብይት (Stock
Market) ላይ
በነበረው ተዕጽኖ መቶ ሰላሳ በሊየን ዶላር
የሚገመት ኪሳራ አድርሷል። በቅርብ ጊዜ ቢቢሲ
የዘገበውም በሜክሲኮ ሃገር በዋትሳፕ (WhatsApp) ልጆችን
አግትዋል ተብሎ በተላለፈው ሃሰተኛ መረጃ
ምክኒያት በተቀሰቀሰ ቡድን ሁለት ግለሰቦች
በእሳት ተጋይተው ሂወታቸው ሊያልፍ ችሏል።
አንዳንድ ጊዜ በተለያየ ሃገር በሚኖረው
የፖለቲካ አለመረጋት ወቅትም በሶሺያል ሚዲያ
የሚሰራጭ ሃሰተኛ መረጃ ሊያደርስ የሚችለውን
ቀውስ ስናስብ ምናልባት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ
ሊያመዝን ይችላል ብንል አይፈረድብንም።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ