ባሁኑ ጊዜ ሁላችንም ይሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚ ነን። የምንመገበው ምግብ የምንለብሰው ልብስ የምንገለገልበት መጓጓዣ የምንገናኝበት ስልክ የምንኖርበት ህንፃ የምንመለከተው ቴሌቪዥን የምንውጠው መድሓኒት፤ ሁልም ይሳይንስ ውጤቶች ናቸው። ምንም ማምለጫ በሌለው ዓይነት እያንዳንዱ የህይወታችን እንቅስቃሴ ከስይንስ ውጤት ጋር የተቆራኘ ነው። እንዲህ ሆኖ ሳለ ሳይንስን አለማወቅ ወይም አለማሰብ ያዛልቅ ይሆን? በመጀመሪያ ደረጃ በተፈጥሮአችን የማናውቀውን ነገር የመጠርጠርና የመፍራት ባህርይ አለን፤ ስለዚህም ሊጠቅመን የሚችለውን በዓይነቁራኛ ተመልክተን ብቻ ማለፍን ልንመርጥ እንችላለን። በሌላ በኩል ደግሞ አንድን ነግር በደንብ ሳንረዳ መጠቀሙ ለሱ ውይም ለአምራቹ ተገዥ ሊያረገን ይችላል። ሳይንስና ተክኖሎጂን ባለመረዳት በሌሎች ልንታለል ወይም ተዕጽኖአቸው ሥር ልንገባ እንችላለን። በዚህ ዓይነት ብንቀበር እንኳ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች መገለል በማንችልበት ሁኔታ እያለን፤ ከላይ በተጠቀሱትና ከቀን እስተቀን በሚገጥሙን በሌሎች ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ውሳነዎች ማረግ ይጠበቅብናል። ከራሳችን ውስጥ ከሚተራመሱት ሃሳቦች በተጨማሪም የተለያየ ምክር ከተለያየ አቅጣጫ የደርሰናል። ከዘመድ ከጓደኛ ከስራ ባልደረባ ከብዙሃን መገናኛና አሁን ደግሞ ከድህረ መረብ። ብዙ ጊዜ ምክሩም ጠቃሚ ሊሆን ቢችልም ብዚያው መጥን ደግሞ እርስ በርሱ የሚቃረንና የሚያምታታ ሊሆን ይችላል። ያም ሆን ይህ ከውሳኔያችን ተነስተን የምንፈጽመው ድርጊት የሚያስከትለው ውጤት የሞት የሽረት ያህል ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ህመም ሲገጥመን የባህል ወይስ ዘመናዊ ህክምና መምረጥን። እንዲሁም በሃላፊነት ቦታ ያሉ ደግሞ ውሳኔዎቻቸው የማህረሰቡ ደህንነት ላይ ተዕጽኖ ሊኖራቸው ይችላል። አሁንም ለምሳሌ ያህል ሰሞኑን በዓልም አቀፍ ደረጃ ጭንቀት እየፈጠረ ያለው የምድር አማካይ የሙቀት መጠን መጨመርን ለመግታት መውሰድ ስላለብን እርምጃዎች። ስለነዚህ መሰል ጉዳዮች ዓቅማችን በሚችለው ያህል ትክክለኛ ውሳኔዎችን ለመፍረድ የምንችለው እውነተኛነታቸው የተፈተኑ መረጃዎችን አንድ በአንድና በቅደም ተከተል አመዛዝነን ሲሆን ብቻ ነው። ቀደም ሲል እንደገለጽኩትም በሙከራ የተፈተኑና የተደራጁ ዕውቀቶች፤ ከነዚህም ዕውቀቶችም ተነስተን ለምንሰራቸው ተግባራት የሚያስከትሉትን ውጤት መተንበይ የሚያስችሉን፤ በሳይንስ ሂደት የተገኙት ዕውቀቶች ናቸው።
ገፆች
ቅዳሜ 30 ሜይ 2015
ቅዳሜ 23 ሜይ 2015
ሳይንስ ምንድነው
ሳይንስ የሚለው ቃል ትርጓሜን በድህረ መረቡ ዊኪፒዲያ በተባለው ሰፊ የጽሁፎች መድረክ ላይ የተመዘገበውን ለመተርጎም ብሞክር፤ ከላቲኑ ሳየንቲያ ወይም ዕውቀት ከሚለው የመጣ ሲሆን ሳይንስ ተፈጥሮንና የተፈጥሮ ክስተቶችን የሚያብራሩና የሚተነብዩ፤ በሙከራ ሊረጋገጡ የሚችሉ ዕውቀቶችን የሚገነባና የሚያደራጅ ጥረት ነው ። ከዚህ ቀደም ሲል የሳይንስ ትርጉም ራሱ የዚህ(ስለ ተፈጥሮ ያለን) ዕውቀት ስብስብን የሚያመለክት የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ጊዜ የቃሉ አጠቃቀማችን ደግሞ እነዚህ ዕውቀቶችን ለማግኘት የምንጠቀማቸውን ስልቶችንም ያጨምራል።
ይህን ትርጉም ለመረዳት አንድ ምሳሌ ልጠቀም። የመሬት ስበት የተለያዩ አካሎች እንቅስቃሰ ላይ ያለውን ተጽኖ ተመልክተን፤ የተለያየ ክብደት ያላቸው አካላት ከተመሳሳይ ከፍታ ወደ መሬት ቢለቀቁ ምድር ላይ እስኪያርፉ ድረስ የሚያልፈው ሰዓት አይለያይም ብለን ልንገምት እንችላለን። ይህም ግምታችን ትክክል ለመሆኑ ማስረጃ እንዲሆነን የተለያዩ አካሎችን ከከፍታ ላይ እየለቀቅንና ምድር እስኪደርሱ የሚያልፈውን ሰዓት እየለካን መሞከር እንችላለን። አንጋፋውም የአስራሰባተኛው ክፍለዘመን ሳይንቲስት ጋሊሊዮም ይህን መሰል ሙከራ ካዘነበለ ህንፃ ላይ የተለያዩ ክብደት ያላቸው ኳስ መሳይ ከብረት የተሠሩ የመድፍ ጥይቶችን በመጣል ሙከራ እንዳካሄደ ተዘክሯል። ሙከራው በገመትንው መሠረት ስኬታማ ቢሆን የመሬት ስበት ባህርይን አውቀናል ልንል እንችል ይሆናል። ከዚህም ዕውቀታችን ተነስተን አንድ አካል በተወሰነ ፍጥነትና አቅጣጫ ብንወነጭፍ፤ ከመነሻው ተነስቶ ምድር ላይ የሚያርፍበት ርቀትንና የሚያልፈውን ሰዓት ልንተነብይ እንችላለን። አሁንም በሙከራ ትንባዬያችን ከተረጋገጠ እውነትም በትክክል የመሬት ስበትን ባህርይ ተረድተናል ማለት ያስችለናል። የሳይንስ ሂደት ግን እዚህ ላይ አያበቃም። ይህን ዕውቀት ለህብረተሰቡ ማሳወቅ ይኖርብናል። ማብራሪያውን የተመለከቱ የተወሰኑ ሰዎች ሙከራዎቹ ላይ እንከን ለማውጣት ይሞክራሉ። በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ አካላትና በተለያዩ የልኬት መሣሪያ ሙከራዎቹን ይደግማሉ። የመጀመሪያ ሙከራው ልይ እንከን ከጠፋና ተጨማሪ ሙከራዎቹ ግኝቶቹን ካስተባበሉ፤ የመሬትን ስበት የሚገልጽ ትክክለኛ ዕውቀት አለን ማለት ነው።
በእርግጥ ሌሎች የዕውቀት ማግኝዎች እንዳሉ እናውቃለን። ከልምድ የሚገኙ ዕውቀቶች አሉ። ከአፈታሪክ የሚገኙም ዕውቀቶች አሉ። እነዚህ ዕውቀቶች ግን በሙከራ የተፈተኑ አይደሉም። በዚህ ዓይነት ከተገኙ ዕውቀቶችም ተነስተን ለሎች ክስተቶችን መተንበይ ያዳግተናል። የዕውቀቶቹ አመሠራረት ላይ ያለን ውስን የሆነ ግንዛቤ ደግሞ ዕ ውቀቶቹን የተለያዩ ሥራዎች ላይ ከማዋል ያቅበናል።
ይህን ያህል የሳይንስ ትርጉምንና ከሳይንስ ሂደት ልናገኛቸው የምንችለውን የዕውቀት ዓይነቶች ካብራራሁ፤ በሚቀጥለው ደግሞ ከሳይንስ ጋር የተያያዘ ሙያ ያላቸው ወይም የሳይንስ ትምህርት ልይ የተሰማሩ ብቻ ሳይሆኑ፤ ሁሉም የህብረተሰባችን አባሎች የመሠረታዊ የሳይንስ ዕውቀት ባለቤት መሆን አስፈላጊነትን ለማስረዳት እሞክራለሁ።

ሐሙስ 14 ሜይ 2015
የጦማሩ ዓላማ
የዚህ ጦማር ዓላማ በሃገራችን ኢትዮጵያ ስይንስ ነክና ከሳይንስ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ርዕሶች ለመዳሰስ ይሆናል። በአማርኛ ቋንቋ ኮምፒዩተር ልይ መጻፍ ፈታኝ ሆኖ ስላገኘሁት ለጊዘው ጦማሩ ገና ሙከራ ለይ እንደሆነ መታየት ይኖርበታል። መልካም ንባብ።
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)