ሳይንስ የሚለው ቃል ትርጓሜን በድህረ መረቡ ዊኪፒዲያ በተባለው ሰፊ የጽሁፎች መድረክ ላይ የተመዘገበውን ለመተርጎም ብሞክር፤ ከላቲኑ ሳየንቲያ ወይም ዕውቀት ከሚለው የመጣ ሲሆን ሳይንስ ተፈጥሮንና የተፈጥሮ ክስተቶችን የሚያብራሩና የሚተነብዩ፤ በሙከራ ሊረጋገጡ የሚችሉ ዕውቀቶችን የሚገነባና የሚያደራጅ ጥረት ነው ። ከዚህ ቀደም ሲል የሳይንስ ትርጉም ራሱ የዚህ(ስለ ተፈጥሮ ያለን) ዕውቀት ስብስብን የሚያመለክት የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ጊዜ የቃሉ አጠቃቀማችን ደግሞ እነዚህ ዕውቀቶችን ለማግኘት የምንጠቀማቸውን ስልቶችንም ያጨምራል።
ይህን ትርጉም ለመረዳት አንድ ምሳሌ ልጠቀም። የመሬት ስበት የተለያዩ አካሎች እንቅስቃሰ ላይ ያለውን ተጽኖ ተመልክተን፤ የተለያየ ክብደት ያላቸው አካላት ከተመሳሳይ ከፍታ ወደ መሬት ቢለቀቁ ምድር ላይ እስኪያርፉ ድረስ የሚያልፈው ሰዓት አይለያይም ብለን ልንገምት እንችላለን። ይህም ግምታችን ትክክል ለመሆኑ ማስረጃ እንዲሆነን የተለያዩ አካሎችን ከከፍታ ላይ እየለቀቅንና ምድር እስኪደርሱ የሚያልፈውን ሰዓት እየለካን መሞከር እንችላለን። አንጋፋውም የአስራሰባተኛው ክፍለዘመን ሳይንቲስት ጋሊሊዮም ይህን መሰል ሙከራ ካዘነበለ ህንፃ ላይ የተለያዩ ክብደት ያላቸው ኳስ መሳይ ከብረት የተሠሩ የመድፍ ጥይቶችን በመጣል ሙከራ እንዳካሄደ ተዘክሯል። ሙከራው በገመትንው መሠረት ስኬታማ ቢሆን የመሬት ስበት ባህርይን አውቀናል ልንል እንችል ይሆናል። ከዚህም ዕውቀታችን ተነስተን አንድ አካል በተወሰነ ፍጥነትና አቅጣጫ ብንወነጭፍ፤ ከመነሻው ተነስቶ ምድር ላይ የሚያርፍበት ርቀትንና የሚያልፈውን ሰዓት ልንተነብይ እንችላለን። አሁንም በሙከራ ትንባዬያችን ከተረጋገጠ እውነትም በትክክል የመሬት ስበትን ባህርይ ተረድተናል ማለት ያስችለናል። የሳይንስ ሂደት ግን እዚህ ላይ አያበቃም። ይህን ዕውቀት ለህብረተሰቡ ማሳወቅ ይኖርብናል። ማብራሪያውን የተመለከቱ የተወሰኑ ሰዎች ሙከራዎቹ ላይ እንከን ለማውጣት ይሞክራሉ። በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ አካላትና በተለያዩ የልኬት መሣሪያ ሙከራዎቹን ይደግማሉ። የመጀመሪያ ሙከራው ልይ እንከን ከጠፋና ተጨማሪ ሙከራዎቹ ግኝቶቹን ካስተባበሉ፤ የመሬትን ስበት የሚገልጽ ትክክለኛ ዕውቀት አለን ማለት ነው።
በእርግጥ ሌሎች የዕውቀት ማግኝዎች እንዳሉ እናውቃለን። ከልምድ የሚገኙ ዕውቀቶች አሉ። ከአፈታሪክ የሚገኙም ዕውቀቶች አሉ። እነዚህ ዕውቀቶች ግን በሙከራ የተፈተኑ አይደሉም። በዚህ ዓይነት ከተገኙ ዕውቀቶችም ተነስተን ለሎች ክስተቶችን መተንበይ ያዳግተናል። የዕውቀቶቹ አመሠራረት ላይ ያለን ውስን የሆነ ግንዛቤ ደግሞ ዕ ውቀቶቹን የተለያዩ ሥራዎች ላይ ከማዋል ያቅበናል።
ይህን ያህል የሳይንስ ትርጉምንና ከሳይንስ ሂደት ልናገኛቸው የምንችለውን የዕውቀት ዓይነቶች ካብራራሁ፤ በሚቀጥለው ደግሞ ከሳይንስ ጋር የተያያዘ ሙያ ያላቸው ወይም የሳይንስ ትምህርት ልይ የተሰማሩ ብቻ ሳይሆኑ፤ ሁሉም የህብረተሰባችን አባሎች የመሠረታዊ የሳይንስ ዕውቀት ባለቤት መሆን አስፈላጊነትን ለማስረዳት እሞክራለሁ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ