ገፆች

ቅዳሜ 30 ሜይ 2015

ለሁሉም ሰው ሳይንስን ማወቅ ለምን ይጠቅማል

ባሁኑ ጊዜ ሁላችንም ይሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚ ነን። የምንመገበው ምግብ፣ የምንለብሰው ልብስ፣ የምንገለገልበት መጓጓዣ፣ የምንገናኝበት ስልክ፣ የምንኖርበት ህንፃ፣ የምንመለከተው ቴሌቪዥን፣ የምንውጠው መድሓኒት፤ ሁልም ይሳይንስ ውጤቶች ናቸው። ምንም ማምለጫ በሌለው ዓይነት እያንዳንዱ የህይወታችን እንቅስቃሴ ከሳይንስ ውጤት ጋር የተቆራኘ ነው። እንዲህ ሆኖ ሳለ ሳይንስን አለማወቅ ወይም አለማሰብ ያዛልቅ ይሆን? በመጀመሪያ ደረጃ በተፈጥሮአችን የማናውቀውን ነገር የመጠርጠርና የመፍራት ባህርይ አለን፤ ስለዚህም ሊጠቅመን የሚችለውን በዓይነቁራኛ ተመልክተን ብቻ ማለፍን ልንመርጥ እንችላለን። በሌላ በኩል ደግሞ አንድን ነገር በደንብ ሳንረዳ መጠቀሙ፣ ለሱ ውይም ለአምራቹ ተገዥ ሊያረገን ይችላል። ሳይንስና ተክኖሎጂን ባለመረዳት በሌሎች ልንታለል ወይም ተዕጽኖአቸው ሥር ልንገባ እንችላለን። በዚህ ዓይነት ብንቀበር እንኳ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች መገለል በማንችልበት ሁኔታ እያለን፤ ከላይ በተጠቀሱትና በለሎች ከቀን እስተቀን በሚገጥሙን ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ውሳነዎች ማረግ ይጠበቅብናል። ከራሳችን ውስጥ ከሚተራመሱት ሃሳቦች በተጨማሪም የተለያየ ምክር ከተለያየ አቅጣጫ የደርሰናል። ከዘመድ ከጓደኛ ከስራ ባልደረባ ከብዙሃን መገናኛና አሁን ደግሞ ከድህረ መረብ። ብዙ ጊዜ ምክሩም ጠቃሚ ሊሆን ቢችልም ብዚያው መጥን ደግሞ እርስ በርሱ የሚቃረንና የሚያምታታ ሊሆን ይችላል። ያም ሆን ይህ ከውሳኔያችን ተነስተን የምንፈጽመው ድርጊት የሚያስከትለው ውጤት የሞት የሽረት ያህል ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ህመም ሲገጥመን የባህል ወይስ ዘመናዊ ህክምና መምረጥን። እንዲሁም በሃላፊነት ቦታ ያሉ የሚያረጓቸው ውሳኔዎቻቸው የማህረሰቡ ደህንነት ላይ ተዕጽኖ ሊኖራቸው ይችላል። አሁንም ለምሳሌ ያህል ሰሞኑን በዓልም አቀፍ ደረጃ ጭንቀት እየፈጠረ ያለው የምድር አማካይ የሙቀት መጠን መጨመርን ለመግታት መውሰድ ስላለብን እርምጃዎች። ስለነዚህ መሰል ጉዳዮች ዓቅማችን በሚችለው ያህል ትክክለኛ ውሳኔዎችን ለመፍረድ የምንችለው እውነተኛነታቸው  የተፈተኑ መረጃዎችን አንድ በአንድና በቅደም ተከተል አመዛዝነን ሲሆን ብቻ ነው። ቀደም ሲል እንደገለጽኩትም በሙከራ የተፈተኑና የተደራጁ ዕውቀቶች ተመሥርተን፤ ከነዚህም ዕውቀቶችም ተነስተን የምንፈጽማቸው ተግባራት የሚያስከትሉትን ውጤት መተንበይ የሚያስችሉን፤ በሳይንስ ሂደት የተገኙት ይበልጥ አስተማማኝ ናቸው።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ