ይህን ልትፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ የዘመናዊ ህክምና ትምህርት ዲግሪ ባለቤት ከመሆኔ ዘንድ ስመለከት፣ በለፉት ዓመታት ለበርካታ ህሙማን የታይፈስና የታይፎይድ በሽታዎች እንደተገኙባቸውና ከነዚህም በሽታዎች ለመፈወስ የሚያስፈልጉትን አንቲባዮቲክ የተባሉ መድሓኒቶች ሲታዘዝ በመታዘቤ ነው። ዘመናዊ ህክምና ከባህላዊ ህክምና የሚለይው በዋነኛነት ዘመናዊው ህክምና ሳይንስ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ነው። ይህም ማለት የህመሙን ዓይነት ለይቶ ለማውቅ፤ ህመሙ ሰውነት ላይ ያስከተለውን በደል ለመረዳት፤ ለህመሙ የሚደረገውን የህክምና እርምጃ ለመወሰን፤ የህመምተኝው ወደፊት ዕጣ ፋንታ መገመትን የመሳሰሉት በሳይንሳዊ ምርምር በተገኙ መረጃውች ላይ የተመሰረቱ ምሆን የኖርባቸዋል። ይህን ካልን ስለ ታይፈስና ታይፎይድ ሳይንስ ምን ይነግረናል?
በመጀመሪያ ታይፈስን ብንመለከት - ታይፈስ በአንዲት ውስን ዓይንት በለምድ ጀርም በለን ከምንጠራቸው አንዱ (ሳይንሳዊ ስያሜው ሪኬትሲያ ፕሮዋዜኪአይ - Rickettsia prowazekii) የሚከሰትና በሰውነት ቅማል ዓማካይነት የሚተላለፍ የህመም ዓይነት ናው። ይህም ህመም ዋነኝው ምልክቱ ድንገተኛና ከፍተኛ ትኩሳት ሲሆን በተጨማሪ ከባድ ራስ ምታትና ሌሎችም ምልክቶች ይኖረዋል። ብዙውን ጊዜ የሚከሰተውም ቅማል ከሰው ወደሰው ሊዛመት በሚችልባቸው ንጽህና በጎደለባቸውና በተጣበቡ ሁኔታዎች - ለምሳሌ በወይኒ ቤቶች፣ ጎዳና ተዳዳሪዎች መጠለያ የመሳሰሉት ነው። ህመሙም ሲከሰት በአብዛኛውም ጊዜ አንድ ነጠላ ሰው ብቻ ላይ ሳይሆን የሚታየው በአጭር ቀናት ውስጥ በጥቂት ግለሰቦች ላይ ወይም በወረርሺኝ መልክ ይሆናል። እነዚህን ሁሉ ግምት ውስጥ ከተን ባአንድ ጥሩ ኑሮ ደረጃ ላይ ያለና ንጽህናው የተጠበ ግለሰብን ታይፈስ አለብህ ሲባል ጥርጣሬ አያስነሳም ወይ።
ታይፎይድን ስንመለከት ደግሞ አሁንም በአንድ ውስን ጀርም (ሳልሞኔላ ታይፊ - Salmonella typhi) አማካይነት የሚከሰት ተላላፊ በሽታ ሲሆን፣ የሚተላለፈው ባዓይነ ምድር በተበከለ ውሃ ወይም የምግብ ዓይነቶች አማካይንት ነው። ምልክቶቹም አሁንም ከፍተኛ ትኩሳትና ራስ ምታት ሲገኙባቸው እንዲሁም የሆድ ህመም፣ የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ ሊኖሩ ይችላሉ። የሚተላፈው በተበከለ ውሃ ወይም ምግብ ስለሆን ግን የታይፈሱን ያህል የንሮ ደረጃ ላይለይ ይችላል።
እነዚህ ሁለት ህመሞች አንድ ግለሰብ ላይ ለመኖራችው ማረጋገጥ ግን የሚያስቸግርብት ምክኒያት ምልክቶቹ ከሁለቱም መካከልና እንዲሁም ከበርካት ሌሎች በሽታዎች - ለምሳሌ ሃይለኛ ጉንፋን ጋር መመሳሰላቸውና መደራረባችው ነው። በምልክቶቹ ብቻ ለመወሰን ስለሚያስቸግርም የነዚህ ህመሞች መሮር ሲጠረጠር በህክምና ባለሙያዎች በደም ላይ የሚሠሩ ምርመራዎች ይታዘዛሉ (ዊዳል እን ቫይል ፌሊክስ - Widal, Weil Felix)። እነዚህም ምርምራዎች ፖዘቲቭ (Positive) ካሳዩ ከሁለቱ አንዱ ወይም አንዳንድ ጊዜ ሁለቲም ህመሞች ባንድ ጊዜ እንደተከሰቱ በመቁጠር ተገቢው መድሃኒት ይታዘዛል።
ነገር ግን ትልቁ ችግር ካላይ የተጠቀሱት የደም ምርምራዎች የሁለቱንም ህመም መኖርን ማርጋገጥ ችሎታችው በጣም ውስን ከምሆኑ የተናሳ ምናልባት ከንጭራሹ መታዘዝ የለባችውም ያስብላል። ይህንንም ለመረዳት ሙያው ልይ ላልሆን ሰው በጣም ቀላል ባይሆንም በቀጣይ ልጥፎች ከሌሎች የሳይንስ መረጃዎች ጋር በማዛመድ ለመተንተን እሞክራለሁ። ለጊዜው ግን በአጭሩ ምርመራዎቹ በቀጥታ ጀርሞቹ በሰውነት ውስጥ መኖራችውን ወይም አለመኖራቸውን ሳይሆን ይሚነግሩን የተለያዩ ህመሞችን ለመከላከል ብሎ አካላችን የሚያመንጨው አንቲቦዲ (Antibody) የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ነው የሚለኩት። እንዚህ አንቲቦዲዎች ለአንዳንድ ህመሞ ዓይንት ጥሩ እመላካች ቢሆኑም (ለምሳሌ ለኤች አይ ቪ) ለታይፈስና ታይፎይድ ግን በከፈተኛ ደረጃ ህመሙ በሌለባቸው በርካታ ሰዎች የተሳሳተ ማረጋገጫ እንደሚሰጡ ጥናቶች አሳይተዋል። በተለይ ለታይፈስ የሚሠራው ቫይል ፌሊክስ ምርመራ ህመሙ ከሌለባችው መካከል ሃምሳ ከመቶውን የተሳሳተ መረጃ ሊያመለክት እንደሚችል ታይቷል።
ሳይንስና ዘመናዊ ህክምና በከፈተኛ ደረጃ የተጠላለፉ እንደመሆናቸው መጠን ባለሙያዎቹም በሥራቸው ሂደት ይህንን ባይዘነጉ፣ በዘርፉ ያሉት የመንግሰት ቁጥጥር አካሎችም በላብራቶሪ ምርመራ ጥራትና ለሃገራችን ሁኔታ ተገቢነታቸው ላይ ተኩረት ቢሰጥ፤ በህብረተሰቡም ዘንድ ስይንስ ላይ ያለው ግንዛቤን ለማሻሻል ጥረት ቢደረግ ፣ በታይፈስና ታይፎይድ ላይ የታየውንና ሌሎችንም ተመሳሳይ የህክምና አገልግሎት ላይ ሊሠሩ የሚችሉ ስህተቶች መስፋፋትን በበለጠ ለመከላከል ይቻላል።

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ