በዚህ ልጥፍ የደም ግፊት ላይ ተዕጽኖ ያላቸውን ተቀያያሪ ነግሮችን መመልከት እንሞክራለን። በሚቀጥለው ልጥፍ የደም ብዛት ሰውናታችን ከሚገኙ ውህዶች ጋር ያለውን ግንኙነት እናያለን። የደም ብዛት ህመም ስንል በሰውነታችን የሚዘዋወረው የደም መጠን መጨመር ሳይሆን፣ በደም መዘዋወሪይ ቱቦዎች ላይ የሚከሰተው የደሙ ግፊት መጭመርን ያመለክታል። የግፊቱ መጠን በሁለት ዋና ምክኒያቶች ይወሰናል – የመጀመሪያው ልባችን የሚገፋው የደሙ መጠንና ሁለተኛው ደግሞ የደም ስሮቻችን ስፋት ወይም ጥበት ናቸው። ልባችን የሚገፋው የደሙ መጠን በተራው ሁለት ምክኒያቶች ይወስኑታል። የመጀመሪው ለባችን አንድ ጊዜ ሲመታ የሚገፋው የደም መጠንና ሁለተኛው ደግሞ ልባችን የሚመታበት ፍጥነት ነው። ይህን የበለጠ ለመረዳት ከሁሃ ፖምፕ ጋር ማነጻጸር እንችላላን። የፖምፑ ሞተር አንድ ጊዜ ሲዞር ከአንድ የልብ ትርታ፣ የፖምፑ ሞተር በደቂቃ የሚዞረው ፍጥነት ከልባችን ትርታ ፍጥነት፣ የውሃ መተላለፊያ ቧንቧዎች መጠን ደግሞ ከደም ሥሮቻችን ስፋት ይንጻጸራሉ። ስለዚህ እነዚህን ምክኒያቶች የደም ግፊት ላይ ያላቸውን ተእጽኖን ስንመለከት፣ ልብ አንድ ጊዜ ሲመታ የሚገፋው የደም መጠንና የትርታው ፍጥነት ሲጨምሩ፣ እንዲሁም የደም ሥሮቻችን ሲጠቡ የደም ግፊት እንዲጨምር ያረጉታል። ለምሳሌ የአትክልት ውሃ ማጠጫ ጎማን ስንመለከት፣ ቧንቧውን የበለጠ ስንከፍት ወደ ጎማው የሚገባው ይውሃ መጠን ይጨምርና ከጫፉ ሲወጣም የበለጠ ርቀት ይወረወራል። በርቀት የሚገኙትን ለማጠጣት ስንፈልግ ጫፉን በከፊል በጣታችን እንዘጋውና፣ ይህም በጎማው ውስጥ ያለውን ግፊት ስለሚጨምር አሁንም በበለጠ ርቀት ለማፈናጠር ያስችለናል። በጣም ቧንቧውን ከከፈትን ወይም ጫፉን ከልክ በላይ ከደፈንን ጎማው ሊፈነዳም ይችላል። በተመሳሳይ ሁኔታ የደም ሥሮቻችን ጠበው የደሙን ዝውውር ከከለከሉ፣ ደም ሥሮቻችን ሊጎዱና ሊፈነዱ ይችላሉ። በዚህ ዓይነት በአንጎላችን የሚገኙ የደም ሥሮች ሲፈነዱ ስትሮክ ተብሎ የሚጠራውን ህመም ያስከትላል። ስለዚህ ይህን ሰለ ደም ግፊት ካልን፣ ሰውነታችን ውስጥ ካሉት ውህዶች ጋር በምን ዓይነት ይገናኛል? ይህንን በሚቀጥለው ልጥፍ ከአንድ ለደም ብዛት ህመም ከሚሰት መድሃኒት አንጻር እንመለከታለን።
ገፆች
ሰኞ 2 ዲሴምበር 2024
ረቡዕ 26 ጁን 2024
ረቂቁ አቶም (ክፍል 3ለ) - ውህዶች ምን የመስላሉ
አንድን ነገር ለመረዳት ስንፈልግ ካሉን ስሜቶች በከፍተኛ ደረጃ የምንጠቀመው የማየት ችሎታችንን ነው። በተጨማሪም የመስማት የመዳሰስና የመቅመስ ችሎታዎቻችንን እንጠቀማለን። ነገር ግን እንዚህ ችሎታዎቻችን በቀጥታ አቶሞችንን ለመረዳት አልጠቀሙንም። ቀደም ሲል የአቶሞችን መኖር የደረስንበት የአንዳንድ ነገሮችንን ጉልህ ባህርይ በማጥናትና፣ ቀጥለንም የማሰብና የማመዛዘን ችሎታችንን ተጠቅመን፣ እንዴት ቢሆን ነው እንዚህን ባህርዮች ሊፈጠሩ የቻሉት ብለን በመጠየቅ ነው። በዚህም ዓይነት ሁሉም ነገሮች እጅግ በጣም ረቂቅ በሆኑ አቶሞች እንደተሠሩ የደረስንበት።
አቶሞችን መመልከት የሚከለክለን ረቂቅነታቸው ብቻ አይደለም። ምንም ዓይነት እዚህ ጀምሮ እዚህ ያልቃል የምንለው ጠጣር ይዘት የላቸውም። ነገር ግን በውስን መልኩ ለመረዳት፣ አቶሞችን የተለያየ መጠን ያላችው በጣም ትናንሽ እንደ ኳስ ክብ የሆኑ አካላት መቁጠር እንችላለን። ቅጥለንም ኳሶቹን በተለያየ መንገድ በመቀጣጠል ውህዶችን ለመግለጽ መሞከር እንችላለን።
ለምሳሌ ውሃን ብንመለከት፣ አንድ የውሃ ውህድ አንድ ኦክሲጅንና ሁለት ሃይድሮጅን አቶም ይይዛል። ይህንንም እንደሚከተለው መግለጽ ይቻላል።
![]() |
ውሃ |
በዚህ ምስል መሃል ላይ በቀይ ኦክሲጅንን ከጎኑ ደግሞ በነጭ ሁለቱን ሃይድሮጅኖች እናያለን። ሃይድሮጅኖቹ መጠናቸው አንስ እንደሚሉና እንዲሁም ሶስቱ አቶሞች ቀጥ ባለ መስመር ላይ ሳይሆን ሸፈፍ ብለው እንደተቀመጡ እንናስተውላለን።
ሁለት ሌሎች ምሳሌዎች ፕሮፔን የተባለውን የሲሊንደር ጋዝንና በሰውነታችን የሚገኘው ግሉኮዝን ብንመለከት ፕሮፔን ሶስት ካርበንና 6 ሃይድሮጅን የያዘ ውህደት እንደሆነና፣ ግሉኮስ ደግሞ 6 ካርበን 6 ኦክሲጅንና 12 ሃይድሮጅን መያዛቸውን እናያለን።
![]() |
ፕሮፔን |
![]() |
ግሉኮዝ |
እነዚህ ምሳሌዎች አነስ ያሉ ውህዶች ሲሆኑ፣ በሰውነታችን የሚገኙት ግን በመቶዎች ወይም በሽህዎች የሚቆጥውሩ አቶሞችን ሊያካትቱ ይችላሉ። በደማችን ሂሞግሎቢን ተብሎ የሚጠራውና የደም ማነስ ሲኖርብን መጠኑ ቀንሶ የምናገኘው ፕሮቲን ከ4000 በላይ አቶሞችን ያካተተ ውህድ ሲሆን ከታች የምንመለከተውን ቅርጽ የያዘ ነው።
![]() |
ሂሞግሎቢን |
የስብ ውህደት ደግሞ በደማችን ሲለካ ትራይግሊሴራይድ ተብሎ የሚጠራው የሚከተለውን ይመስላል።
![]() |
ትራይግሊሴራይድ |
የነዚህን ውህዶች መጥን ስንመለከት ደግሞ፣ የውሃው ውህድ ካንድ የታይፕ ወረቀት ቅጥነት በሚሆን ወደ 350 ሚሊየኑን ማስቀመጥ ስንችል፣ በዚያው ስፋት ውደ 20 ሚሊየን ሂሞግሎቢን ማስቀመትጥ እንችላለን። ክብደተቸውን ስንመለከት ይውሃው ውህደት በአንድ ግራም ሰላሳ ሺህ ቢሊየን ቢሊየን (3ና 22 ዜሮ) ውህዶች ሲይዝ ዘጠኝ ቢሊየን ቢሊየን (9ና 18ዜሮ) ሂሞግሎቢን ውህዶችችን ማካተት ይችላል።
የደም ማነስ ሲጠረጠር በደማችን የሂሞግሎቢን መጠን የሚለካ ሲሆን፣ ኖርማል በሚሆንበት ጊዜ በአንድ የደም ጠብታ በአማካይ 7.5 ሚሊግራም (የአንድ ግራም አንድ ሺኛ) ሲገኝ፣ ይህም ወደ ስልሳ ሚሊየን ቢሊየን (6ና 16 ዜሮ) ውህዶችን ያካትታል።
በሰውነታችን የሚገኙ ውኡህዶችን ከላይ ባየነው መልክ የንጥረ ነገር ይዘታቸውንንና እንዲሁም ቅርጻቸውን በሚገባ የመረዳት አስፈላጊነቱን ደግሞ በሚቀጥለው ልጥፍ እንመለከታለን።
ረቡዕ 22 ሜይ 2024
ረቂቁ አቶም (ክፍል 3ሃ) - ሂወት ሰጭ አቶሙ ካርበን
ከ19ኛው ክፍለ ዘመን በፊት ሂወት ያላቸው ፍጡሮች በልዩ ሂወት ሰጭ ሃይል አማካይነት ንጥረ ነገሮችን በማዋሃድ ኦርጋኒክ የተባሉ ውህዶችን ይገነቡ እንደነበረ ይታመን ነበር። ንጥረ ነገሮቹ መካከል ካርበን በዋነኛነት አስፈላጊ ሲሆን፣ በተጨማሪም ሃይድሮጅን፣ ናይትሮጅን፣ ኦክሲጅንና እንዲሁም አነስ ባሉ መጠኖች ሰልፈር፣ ፎስፎረስ እና ሌሎችም ይገኙባቸዋል። በጊዜው እነዚህ ኦርጋኒክ የተባሉ ውህዶች ሂወት ባለቸው ፍጡሮች ብቻ ሊሠሩና ከዚህ ውጭ ግን በተለመዱት የኬሚካል የማዋሃድ ዘዴዎች መሥራት እንደማይቻል ይታመን ነበር።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1824 ፍሪድሪክ ሆለር የተባለ ሳይንቲስት ኦክዛሊክ አሲድ የተባለውንና እስከዚያ ድረስ እንደ ኦርጋኒክ ይታይ የነበረውን ውህድ በላብራቶሪ በመሥራት፣ እንዲሁም በ1828 ዩሪያን (አው የማዳበሪያው) በመስራቱ፣ እንዲሁም ከዚያ በኋላ የተለያዩ ሳይንቲስቶች ከነዚህም የበለጡ ውስብስብ የሆኑ ውህዶችን በላብራቶሪ በመሥራታቸው፣ ልዩ ሂወት ሰጭ ሃይል በፍጡርሮች ውስጥ የመገኘቱን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል።
ምንም እንኳ ካርበን የተለየ ነፍስ ሰጭ ሃይል ወይም ንጥረ ነገር ባይሆንም፣ ነፍስ ያላቸው የሚገነቡበት ውህዶች ሁሉ ካርበነን መሠረት ያረጉ ሲሆን፣ ካርበንም ለዚህ ተግባር ተስማሚ የሚያረጉት ልይ ባህርዮች አሉት። ከነዚህ ባህርዮች ዋናዎቹ ከሌሎች ንጥረ ነገሮች በቀላሉ ውህደት የመፍጠር ችሎታውና፣ የካርቦን አቶሞች እርስ በእርስ በመገጣጠም ረጅም ሰንሰለቶችንና ቀለበቶችን የመሥራት ችሎታው ይገኙባቸዋል። እንዚህ ካሮበንን መሠረት አርግው ሒውት ያላቸውን ሁሉ የሚገነቡት እነማን ናችው ብለን ብንጠይቅ፣ ከምንመገባቸው ይዘት በተያያዘ ስማቸው ሲጠራ የምንሰማው ካርቦሃይድሬት ቅባትና ፕሮቲን ሆንው እናገኛቸዋለን። ቀደም ባለ ልጥፍ ንጹህ ካርቦን በጥላሸት፣ በአልማዝ እንዲሁም በእርሳስና ባትሪ ድንጋይ ውስጥ ግራፋይት ተብሎ በሚጠራ መልኩ እንደሚገኝ ተመልክተናል። ይህ ራሱ ካርቦን ከሌሎች ንጥረ ነገሮችና እርስ በእርሱ በመዋሃድና በመደራጀት ሂወት ላላችው ሁሉ መሠረታዊ ሆኖ እናገኘዋለን! አንድ ሌላ እጅግ አስደናቂ አሁንም ካርበን ላይ የተመሠረተ ሒውት ባለችው ሁሉ የሚገኝ ውህድ መጥቀስ ይቀረናል። ይህም ዲኤንኤ ይተባለው ሲሆን በዘር የሚተላለፉ ባህረዮችን መረጃ በአቶሞቹ አወቃቀር የያዞ የምናገኘው ነው።
በዚህ ዓይነት አንድ ፍጡር የገነቡትን ውህዶችንና አቶሞችን ነጥለን የመለያየት ችሎታ ቢኖረን፣ የተለእያየ መጠን ሃይድሮጅን፣ ናይትሮጅንና፣ ኦክሲጅን ጋዞችን፣ እንዲሁም እንደፍጡሩ ዓይንት ይተለያየ መጠን ያልው ይጥላሸት መሰል ክምር እናገኛለን። እንዚህ ተናጠል ንጥረ ነገሮች ሂወት አልባ ከሆኑ ነገሮች ከምናገኛችው ምንም ልዩነት የላቸውም። ነገር ግን በተለያዩ ውህደቶችና መዋቅሮች ሲደራጁ፣ ሂወት ባላቸው ፍጡሮች የምንመለከታቸውን ባህርዮች ሲያመነጩ እንታዘባለን።
ስለ አቶምና ሒውት ይህን ያህል ካልን፣ በቀጣዩ ልጥፍ አቶሞችንና ውህዶችን ለመረዳት የሚያስችሉንን የምስል አይነቶች እንመለከታለን።