ገፆች

ረቡዕ 22 ሜይ 2024

ረቂቁ አቶም (ክፍል 3ሃ) - ሂወት ሰጭ አቶሙ ካርበን

 

19ኛው ክፍለ ዘመን በፊት ሂወት ያላቸው ፍጡሮች በልዩ ሂወት ሰጭ ሃይል አማካይነት ንጥረ ነገሮችን በማዋሃድ ኦርጋኒክ የተባሉ ውህዶችን ይገነቡ እንደነበረ ይታመን ነበር። ንጥረ ነገሮቹ መካከል ካርበን በዋነኛነት አስፈላጊ ሲሆን፣ በተጨማሪም ሃይድሮጅን፣ ናይትሮጅን፣ ኦክሲጅንና እንዲሁም አነስ ባሉ መጠኖች ሰልፈር፣ ፎስፎረስ እና ሌሎችም ይገኙባቸዋል። በጊዜው እነዚህ ኦርጋኒክ የተባሉ ውህዶች ሂወት ባለቸው ፍጡሮች ብቻ ሊሠሩና ከዚህ ውጭ ግን በተለመዱት የኬሚካል የማዋሃድ ዘዴዎች መሥራት እንደማይቻል ይታመን ነበር።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1824 ፍሪድሪክ ሆለር የተባለ ሳይንቲስት ኦክዛሊክ አሲድ የተባለውንና እስከዚያ ድረስ እንደ ኦርጋኒክ ይታይ የነበረውን ውህድ በላብራቶሪ በመሥራት፣ እንዲሁም በ1828 ዩሪያን (አው የማዳበሪያው) በመስራቱ፣ እንዲሁም ከዚያ በኋላ የተለያዩ ሳይንቲስቶች ከነዚህም የበለጡ ውስብስብ የሆኑ ውህዶችን በላብራቶሪ በመሥራታቸው፣ ልዩ ሂወት ሰጭ ሃይል በፍጡርሮች ውስጥ የመገኘቱን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል።

ምንም እንኳ ካርበን የተለየ ነፍስ ሰጭ ሃይል ወይም ንጥረ ነገር ባይሆንም፣ ነፍስ ያላቸው የሚገነቡበት ውህዶች ሁሉ ካርበነን መሠረት ያረጉ ሲሆን፣ ካርበንም ለዚህ ተግባር ተስማሚ የሚያረጉት ልይ ባህርዮች አሉት። ከነዚህ ባህርዮች ዋናዎቹ ከሌሎች ንጥረ ነገሮች በቀላሉ ውህደት የመፍጠር ችሎታውና፣ የካርቦን አቶሞች እርስ በእርስ በመገጣጠም ረጅም ሰንሰለቶችንና ቀለበቶችን የመሥራት ችሎታው ይገኙባቸዋል። እንዚህ ካሮበንን መሠረት አርግው ሒውት ያላቸውን ሁሉ የሚገነቡት እነማን ናችው ብለን ብንጠይቅ፣ ከምንመገባቸው ይዘት በተያያዘ ስማቸው ሲጠራ የምንሰማው ካርቦሃይድሬት ቅባትና ፕሮቲን ሆንው እናገኛቸዋለን። ቀደም ባለ ልጥፍ ንጹህ ካርቦን በጥላሸት፣ በአልማዝ እንዲሁም በእርሳስና ባትሪ ድንጋይ ውስጥ ግራፋይት ተብሎ በሚጠራ መልኩ እንደሚገኝ ተመልክተናል። ይህ ራሱ ካርቦን ከሌሎች ንጥረ ነገሮችና እርስ በእርሱ በመዋሃድና በመደራጀት ሂወት ላላችው ሁሉ መሠረታዊ ሆኖ እናገኘዋለን! አንድ ሌላ እጅግ አስደናቂ አሁንም ካርበን ላይ የተመሠረተ ሒውት ባለችው ሁሉ የሚገኝ ውህድ መጥቀስ ይቀረናል። ይህም ዲኤንኤ ይተባለው ሲሆን በዘር የሚተላለፉ ባህረዮችን መረጃ በአቶሞቹ አወቃቀር የያዞ የምናገኘው ነው።

በዚህ ዓይነት አንድ ፍጡር የገነቡትን ውህዶችንና አቶሞችን ነጥለን የመለያየት ችሎታ ቢኖረን፣ የተለእያየ መጠን ሃይድሮጅን፣ ናይትሮጅንና፣ ኦክሲጅን ጋዞችን፣ እንዲሁም እንደፍጡሩ ዓይንት ይተለያየ መጠን ያልው ይጥላሸት መሰል ክምር እናገኛለን። እንዚህ ተናጠል ንጥረ ነገሮች ሂወት አልባ ከሆኑ ነገሮች ከምናገኛችው ምንም ልዩነት የላቸውም። ነገር ግን በተለያዩ ውህደቶችና መዋቅሮች ሲደራጁ፣ ሂወት ባላቸው ፍጡሮች የምንመለከታቸውን ባህርዮች ሲያመነጩ እንታዘባለን።

ስለ አቶምና ሒውት ይህን ያህል ካልን፣ በቀጣዩ ልጥፍ አቶሞችንና ውህዶችን ለመረዳት የሚያስችሉንን የምስል አይነቶች እንመለከታለን።


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ