ፕሮቲን በፍጡሮች ከሚገኙ ትላለቅ ከሚባሉ ውህዶች አንዱ ሲሆን፣ በሰው አካል ውስጥ ወደ 100000 የተለያዩ የፕሮቲን ዓይነቶች ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል። ከዚህ ቀደም የተመለከትነው ኤንዛይምም ከነዚህ መካከል ሲሆን ጥቂት ሌሎቹን ዳሰስ እናርግ። ከሱ በፊት ግን ስለ ፕሮቲን ውህድ የኬሚካል መዋቅርና ቅርጽ እንመልከት።
ፕሮቲን ብዙ አነስተኛ ውህዶችን በመቀጣጠል ከሚሠሩ ግዙፍ ውህዶች መሃል አንዱ ሲሆን፣ እነዚህ ትናንሽ ውህዶች አሚኖ አሲድ ተብለው ይጠራሉ። ከሚታወቁት ፕሮቲኖች አነስተኛው ታል ፕሮቲን 11 አሚኖ አሲዶች ብቻ የያዘ ሲሆን ትልቁ 34350 አሚኖ አሲድ የያዘው ጡንቻችን ውስጥ የሚገኘው ታይቲን ይባላል።
ሁሉም በተፈጥሮ የምናገኛቸው ፕሮቲኖች የሚገነቡት በ20 ይተለያዩ የአሚኖ አሲድ ብቻ ሲሆን የፕሮቲኖቹ ቅርጽ እና ባህርይ የሚውሰነው ከነዚህ 20 አሚኖ አሲዶች የትኞቹን እንዳካተተና፣ ሲቀጣጠሉ ባላቸው ቅደም ተከተል ይሆናል። አሚኖ አሲዶች ሁሉም በአንድ አይነት አቀማመጥ የተገጣጠሙ 2 ካርበን 2 ኦክሲጀን 1 ናይትሮጀን እና 4 ሃይድሮጅን ሲኖራቸው፣ በአንድ ጎናቸው ግን ባሏቸው የተላያዩ አቶሞች ስብስብ አዱ ከሌላው ይለያል።
አሚኖ አሲዶቹ ሲገጣጠሙ ተለማጭ በሆነ መልክ ሲሆን አቶሞቹ ባላቸው የመገፋፋት ወይም የመሳሳብ ባህርይ መሠረት የአሚኖ አሲድ ሰንሰለቱ በመታጠፍና በመጠላለፍ ፕሮቲኑ የሚይዘውን ቅርጽ ይወስኑታል። ፕሮቲኑ በመጨረሻ የሚይዝው ቅርጽ በሰውነታችን ለሚኖረው ተግባር ወሳኝ እንደሆነ ተመልክተናል። የአንድን ፕሮቲን የአሚኖ አሲዶች ይዘትና ቅደም ተከተል በላብራቶሪ ምርመራዎች አማካይነት ማወቅ በጣም ከባድ ባይሆንም፣ ቅርጹን ግን ለማውቅ ፕሮቲኑን ወደ ፈርጥ መሳይ ይዘት በማጣራትና፣ ኤክስ ሬይ ክሪስታሎግራፊ ተብሎ የሚጠራውን ዘዴ የመጠቀም አድካሚ ሂደት አስፈላጊ ሆኖ እናገኘዋለን። ከአሚኖ አሲድ ቅደም ተከተል ብቻ ተነስተን የፕሮቲኑን ቅርጽ ለመተንበይ 50 ዓመት ያህል ጥረት ሲደረግና፣ የተፈጥሮ ሳይንስ ታላቁ ፈተና እንደተባለ የቆየ ሲሆን፣ በ2018 ዲፕ ማይንድ ተብሎ በሚጠራ ኩባንያ የተሠራው አልፋ ፎልድ የተባለ ኤአይ ፕሮግራም በጥሩ ትክክለኛነት ይህን መተንበይ ችሏል።
አንዳንድ በሰውነታችን የሚገኙ ፕሮቲኖች እንሞልከት
(እነዝህ ምስሎች እያንዳዱን አቶም ከማሳየት ይልቅ ቅለል ባለው ሪበን ሞደል ይጠቀማሉ)
በጥፍርና ጽጊጉራችን የሚገኘው ጠንካራው ኬራቲን
ቆዳችን ሳይጎዳ እንዲለጠጥ እንደ ስፕሪንግ መሳብና መኮማተር የሚችለው ኮላጅን
ሰውነታችን ጀርም መክላከል የሚያስችለን በደማችን ሟምቶ የሚገኘው አንቲ ቦዲ
ዓይናችን ወስጥ የሚገኘው የብርሃን ስሜት የሚያስችለን ረሮዶፕሲን
ረቂቅ አንደ ኮለራ እና ታይፎይድ ያሉ ህመም የሚያስከትሉ ባክቴሪያ በተባሉ ረቂቅ ነፍሳት እንዲዋኙ የሚያስችላቸው አስደናቂ በፕሮቲኖች የተገነባ ሞተርን እንመልከት።
በተለያዩ ፕሮቲኖች የተገነባ ይባክቴሪያ ጭራ ሞተር