እንደ አውራፓውያን አቆጣጠር 1809 የተወለደው እንግሊዛዊው ቻርልስ ዳርዊን (Charles Darwin) በ1831 ተነስቶ ለአምስት ዓመታት ቢግል (Beagle) በተባለች መርከብ ዓለምን ዞረ። በጉዞው ላይ እያለም የተመለከታቸውን ፍጡሮች እና የምድር ገጽታዎችን አስተውሎና በዝርዝር ዘክቦ፣ ከተመለሰም በኋላ ተጨማሪ መረጃዎች ከተለያዩ የህብረተሰቡ አባሎች፣ የእንስሳት አርቢዎችን ጭምሮ ካገናዘበ በኋላ፣ ኦሪጂን ኦፍ ስፒሺስ (Origin of Species) አርስት ያለውን ገናና ጽሁፍ፣ ስለ ተለያዩ የንሰሳት ዘር አመጣጥ የሚገልጸውን ተፈጥሯዊ ምርጫ (natural selection) ጽንሰ ሐሳብ በማሳተም በ1859 ለህዝብ ይፋ አረጉ። በአጭሩ ጽንሰ ሃሳቡ የሚለው ሁሉም ነፍሳት አንድ የጋራ የዘር ግንድ ያላቸው እንደሆነና ዝርያዎች በጊዜ እየተቀየሩ እንደሚሄዱ፣ በአንድ ዝርያ አባሎች መካከል በዘር የሚተላለፉ ልዩነቶች እንዳሉና፣ በርግጅምም ጊዜ ለኑሮ ጠቃሚ የሆኑት ባህሪዎች ከትውልድ ትውልድ እየጨመሩ መጥትው በመጭረሻም አዲስ ዝርያ እስከመፍጠር ሊድርሱ እንደሚችሉ ይገልጻል።
ከባህር ተጉዡ ወደ ገዳሙ አባ ስንሄድ በቼኮዝሎቫኪያ ብሩኖ (Brno) ከተማ በነበረ ገዳም አባ የነበሩት ግሬጎር ሜንዴል (Gregor Mendel) ከ1856 እስከ1863 ወደ 28000 የሚጠጉ የአተር ችግኞችን በማብቀልና በማዳቀል የተለያዩ የተክሎቹ ብህርዮች እንዴት ከትውልድ ትውልድ እንደ ሚተላለፉ አጠኑ። ለምሳሌ ረጅም ተክሎች ከአጭር ተክሎች ጋር ሲዳቀሉ የመጀመሪያ ትውልድ ተክሎች ሁሉም ረጅም ሲሆኑ፣ እነዚህም እርስ በእርስ ሲዳቀሉ ግን ከአራት ሶስቱ ረጅም ሲሆኑ ከአራት አንዱ ብቻ አጭር ይሆናል። ከዚሁም እንደሚከተልው መደምደም ቻሉ።
ዘር የሚተላለፈው ጂን (gene) ብሎ የተራችው ዘረ መል አካሎች ሲሆን፣ እነዚህም ሌእያንዳንዱ ለሚተላለፍ ባህርይ ግልጽ (dominant) እና ድብቅ (recessive) ይዝት አላቸው ዘረ መል ይኖራሉ። ለእያንዳንዱ ቀጣዩ ትውልድ እያንዳንዱ ወላጅ አንድ አንድ ዘረ መል ያሚያዋጣ ሲሆን፣ ለልጁ አንድም ግልጽ ዘረ መል ከደረስው ባህርዩ ይታይበታል ማለት ንው።
![]() |
ይሜንዴሊያን ዘር አስተላለፍ |
እስካሁን እንደተረዳነው በዘር የሚተላለፉ ባህርዮች ከብዙ ትውልዶች በኋላ የተለያዩ ዝርያዎች እስከመፍጠር ሊድርሱ የሚሽሉና፣ ከትውልድ ትውልድ አስተላለፍ ሰራዓታቸውን ነው። ግን ስርዓቱንም ተርድተን እያሉ፣ የባህርዩ መረጃ እንዴት ከትውልድ ትውልድ እንደሚተላለፍ አላወቅንም። ይህን ለማወቅ ያስቻለንም ወደ ትንኝዋ ታሪክ ይወስደዳል። በ1910 ቶማስ ሞርጋን ሃንት (Thomas Morgan Hunt) የተባለ ሳይንቲስት በአሜሪካ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲ፣ ፍራ ፍሬ አካባቢ የሚታዩትን ትንኞች እያራባ የሚተላለፉትን የተለያዩ ባህርዮች ማጥናት ጀመረ። ትንኞቹ ለዚህ ጥናት የተመረጡት ከእጭ እስክ አዋቂ ለመድረስ ከ10 እስከ14 ቀን በቻ ስለሚያስፈልጋቸው (አጭር የትውልድ ዘመን)፣ እነሱን ለማሳደግና ለማራባት ቀላል በመሆኑና በቀላሉ ማይትና መለይት የሚቻሉ ባህርዮች ስላላቸው ነው።
ሌላው ግን በንዚህ ትንኞችና አንዳንድ ሌሎች ነፍሳት፣ በህዋሶቻቸው ውስጥ በማጉያ መነጽር ሊታዩ የሚችሉ ክሮሞዞም (chromosome) የተባሉ አካሎች ላይ የሚታዩ ምልክቶችን፣ ሰውነቸው ላይ ከትውልድ ትውልድ ሚተላለፉ ባህርዮች ጋር ማዛመድ መቻሉ ነው። በትንኞቹ በቀላሉ የሚታዩት እነዚህ አካሎች በሁሉም ነፍሳት ሲኖሩ፣ ለምሳሌ በእኛ ላይ ለመመልከት ለመተግብር ከበድ የሚሉ የላብራቶሪ ዘይቤዎች አስፈላጊ ይሆናሉ። አሁን እዚህ ላይ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፉት ባህርዮች መረጃ በክሮሞሶሞቹ ውስጥ እንዳሚገኙ አረጋገጥን። አሁን የቀረን እንዚህ ባዓይን ይማይታዩ ረቂቅ ክሮሞዞሞቹ ይህን መረጃ በምን አይንት እንደሚይዙና፣ ይህ መረጃም እንዴት ወደይትውልዱ ሊተላለፍ እንድሚችል መረዳት ንው። ይህም ሂደት ወድ አቶምና ውህዶቻችን መለሶ ይወስደናል። በሚቀጥልው ልጥፍ ይህን ያስቻለውን ከፕሮቲኖች ባልተናነሰ እጅግ አስደናቂውን ውህድ (molecule) እንመለከታለን።
