በቀድሞው ልጥፍ በዘር የሚተላሊፉ ባህርዮች መረጃ ክሮሞዞም(chromosome, ሃብለበራሂ) ተብልው በሚጥሩት ህዋሶቻችን ውስጥ ሚግኙ አካላት እንደሚገኙ ተረድተናል። ስንቀጥል ይህ መረጃ በምን መልክ እንደሚገኝ እንዴት ማወቅ እንደተቻለ እንመለከታለን። ክሮሞዞሞች ከሚይዟቸው ንጥረ ነገሮች ቀደም ሲል የተሞለከትንው ፕሮቲን ውህድ ሲገኝ(ሂስቶን የተባለ)፣ የማይቆጥር ያህል የተለያየ ግጽታና ውስብስብናታቸው በዘር ለሚተላለፉ ባህርየች መረጃም በተገነቡበት አሚኖ አሲድ ይዘት ወይም ቅድም ተከተል ተቀርጾ ሊሆን ይችላል የሚል ሃሳብ ወይም ግምት ነብር። በሌላ በኩል እ/አ/አ 1869 ፍሬድሪክ ማይስሸር (Friedrich Miescher) በሰውነታችን ከሚገኙ ህዋሶች ፎስፎረስ የተባለ ኢለመንትን ያካተተና፣ የአሲድ ጸባይ ያለውን ነጥረ ነገር ለይቶ ማጣራት ቻለ። በነዚህ ህዋሶች ውስጥ የሚገኘው ኑክሊይስ በተባለ (ክሮሞዞሞችንም በውስጡ የጠቀለለ) አካልም ስለሚገኝ ኑክሌይክ አሲድ ተብሎ ተጠራ። ቀጥሎም አልብሬክት ኮሴል (Albrecht Kossel) የተባለ ሳይንቲስት ይህ ኑክሌይክ አሲድ ይተገነባው አምስት በተለያዩ ኑክሊዮታይድ ቤዝ (nucleotide base) ተብልው በተጠሩ ንጥረነገሮችን በመቀጣጠል ሲሆን፣ ለዚህም ግኝት ብ1920 ኖቤል ተሸላሚ ሆኗል። ይሁን እንጂ በዘር ለሚተላለፉ እልፍ ባህርዬች መረጃ በእነዚህ 5 ብች ኑክሊዎታይዶች ሊያዝ አይችልም የሚል ግምት ነብር። ከዚህ ሲቀጥል በ1950 እርዊን ቻርጋፍ (Erwin Chargaff) በሁሉም ነፍሳት ኤ(Adenine) የተባለው ኑክሊዮታይድ መጠን ቲ(Thymine) ከተባለው መጠን እኩል እንደሆነና፣ ሲ(Cytosine) የተባለው መጠን ደግሞ ጂ(Guanine) ከሚባልው እኩል እንደሆነ ሊገነዘብ ቻለ። ይህም የሚነግርን በኑክሌይክ አሲዶች ኑክሊዮታይዶቹ ጥንድ ጥንድ ሆነው ተቀምጠው እንዳሉ ሲሆን፣ ሮዛሊንድ ፍራንክሊንድ (Rosalind Franklin) የተባለች ስይንቲስት ካገኘቻቸው የኑክሌዪክ አሲድን ቅርጽን ከሚያሳዩ ምስሎች ጋር በማዛመድ ጄምስ ዋትሰን (James Watson) እና ፍራሲስ ክሪክ (Francis Crick) የተባሉ ሳይንቲስቶች ብ1953 የዲ ኤን ኤ ውህድን አቶሞች መዋክር እና ቅርጽ መደምደም ቻሉ። ይህም ቅርጽ ሲታወቅ ወዲይውኑ በዲ ኤን ኤ አማካይነት በዘር የሚተላለፉ ባህርዮች መረጃ እንዴት ከዘር ወደዘር ሊወርድ እንደሚችልም ግልጽ ሆነ።
![]() |
| የዲ ኤን ኤ ሞሌኪዩል አቶሞችና ጥምዝ መሰላል መልክ CC BY-SA 3.0 |
ዲ ኤን ኤ የተጠመዘዘ መሰላል መልክ ሲኖረው ቋሚዎቹ ኑክሊዮታይዶችን በመቀጣጠል የተሰሩ ሲሆን፣ መወጣጫዎቹ ቅድም የጠቀስናቸው ኑክሊዮታይድ ቤዞችን ከየሁለቱ ቋሚ አንዱ ከአንዱ በመጣመር ቋሚዎቹን ያያይዟቸዋል። የራሱን ግልባጭም ለመስራት ሁለቲ ቋሚዎች ይለያዩና እያንዳንዱ በቋሚው ላይ ካሉት ኑክሊዮታይድ ጋር ሊዛመድ የሚችልውን ኘጠላ ኑክሊዮታይድ በመሳብና በመቀጣጠል፣ አንድ የነበርው ዲ ኤን ኤ ሁለት የሆናል።
የዲ ኤን ኤን ቅርጽ ስንለይ ያሳወቀንም፣ እንዴት አርጎ የራሱን ግልባጭ መልሶና መላልሶ ሊያባዛ እንደሚችል ግልጽ አረገልን። ዲ ኤን ኤ የራሱን ግልባጭ መሥራት አስፈላጊ የሚሆነው አንዳንድ በሰውነታችን ያሉ ህዋሶችን በሚጠፉበት ጊዜ ለመተካት አንዱ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ እርባተ ህዋስ (gamete) በምናመርትበት ጊዜ ነው።
በተለያዩ ነፍሳት የሚገኙት የክሮሞዞሞች ቁጥር እና የዘት ይለያያል። ለማሳሌ እኛን ብንመለከት፣ ሁሉም ሰው 46 ክሮሞዞሞች በ23 ሁለት ሁልት ጥንድ ሆንው ይገኛሉ። ገናና ወይም ደካማ ጂኖችም ጥንዶቹ ላይ አንድ አንድ ተቀምጠው ይገኛሉ። የእርባታ ህዋሶች ስናመርት ጥምሮቹ ተለያይተው፣ እርባታ ህዋሶቹ አንድ አንድ የደርሳቸውና 23 ክሮሞዞሞች ይኖራቸዋል። ማለትም ከናታችን 23 ክሮሞዞምና የያዟችው ጂኖች፣ እንዲሁም ከአባታችን በተምሳሳይ 23 ክሮሞዞሞች እናገኛለን። በዚህ ዓይነት ባህርዮቻችን የ እናታችንን እና የአባታችንን የቀላቀለ ሲሆን፣ በአካላችን ላይ ይታዩ አይታዩ የሚወሰነው የደረሰን ዘረ መል ገናና ውይ ደካማ መሆኑ ይሆናል።
![]() |
| የእኛ 23 ጥንድ ከሮሞዞሞች በማጉያ መነጽር ሲታዩ ከhttps://www.nature.com/scitable/topicpage/dna-is-a-structure-that-encodes-biological-6493050/ |
በሚቀጥልው ልጥፍ በዚህ መልክ ባህርዮቻችን ከትውልድ ወደትውልድ መተላለፉ የሚያስከተለው አንደምታን እንመለከታለን።


ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ